ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ (drbekeleg@gmail.com)
ከ30 ዓመት በፊት በአማራና ትግራይ ህዝብ መሃከል ምንም ግጭት አልነበረም። በአብሮነትና በመልካም ጉርብትና ታሪኩን፤ ባህሉንና እምነቱን እየተጋራ ተሳስሮ ለሺዎች ዓመታት በሰላም የኖረ ህዝብ ነዉ። የወያኔ/ኢሕአዴግ አምባገነን ሥርዓት ግን ህዝቡን ከፋፍሎ ለመግዛት ሲል ይህንን መልካም ግንኙነት ለመበጠስ መርዙን ረጨ።
የኢትዮጵያ ህዝብ (በተለይ አማራዉ) ተጨፈጨፈ፤ ተፈናቀለ፤ መከነ፤ ቁም ስቅሉን አየ። ከ7 ወራት በፊት ደግሞ ሕግ ለማስከበር በተባለዉ ዘመቻ/ጦርነት ብዚ የትግራይ ህዝብ ሰለባ ሆነ፤ ብዙ ችግር ደረሰ። እነዚህ ሁሉ እልቂቶች እንዲቆሙ ብዙ ጩኼቶች ስናሰማ ሰነበትን።
መልዕክቴ ቀላል ነዉ። ችግራችን የመሬት ጥበት አይደለም። አንዱ ጎሣ የሌላዉ ጎሣ ጠላት ሆኖ አይደለም። ችግራችን አምባገነን መንግሥታት ናቸዉ፤ ሰላምና እርጋታ ማጣት። ስለዚህ በሚከተሉት ነጥቦች የምንስማማ ከሆነ መልካም ጥረት እናድርግ።
ሀ) የአማራዉና የትግራይ ህዝብ እርስ በርሱ ቢጋጭ ተያይዞ መጥፋትን እንጂ ሌላ ጥቅም አያመጣም። አምባገነን ሥርዓቶች ህዝብን ከፋፍለዉ ለመግዛት በሚፈልጉት ወጥመድ ዉስጥ እንዳንገብ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።
ለ) እግዚአብሔር የሰጠን መሬታችን ሰፊ ነዉ። ጠፉን መሬት እያለማን፤ የቀረዉን በመንከባከብ እንደወትሮአችን የህዝባችንን ደህንነትና አንድነት ማስጠበቅ እንችላለን።
ሐ/ አላስፈላግ የርስ በርስ ግጭት ስንፈጥር ተጠቃሚዉ ሰይጣን ብቻ ይሆናል፤ የዉስጥ ጽንፈኞችና የዉጪ ጠላቶች።
መ/ አንድነታችንን አጠናክረን፤ ተቀባይነት ያለዉን ሕገ መንግሥት አርቅቀን፤ ነፃ ተቁዋማትን ዘርግተን፤ የዲሞክራሲ ሥርዓት ገንብተን፤ ሰላም ብናወርድ ይሻላል።
ፈጣሪያችን ይጨመርበት።