የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት ሠራተኞች ህግ በማስከበር ሂደቱ መረጃ በትክክልና በታማዓኒነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መረጃ አድርሰዋል ብለዋል።
ጦርነቱ የፍትህና የመገፋት ጦርነት ነበር፤ ተገፍተንም ስለነበር ድል አድርገናል።
አሁን ዓላማ አለን በርካታ ሥራአጥ ወጣት አለን፣ የልማት ሥራ እንሰራለን።
ጦርነቱ ለችግር ደራሽነቱን፣ ጀግንነቱንም ያሳየበት ነው፣ ጋዜጠኞች መረጃ በትክክል በማድረስ ሚናቸውንም ተወጥተዋል ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩም ለድርጅቱ ሠራተኞች ሽልማት አበርክተዋል፡፡