ያኔ ነው ! ልብ የሚረካ (ዘ-ጌርሣም)

November 23, 2020

ቀን ያጎደለው በቀን ሲተካ
ያኔ ነው ልብ የሚረካ
ንጋት አይሉት ጨለማ
ጭጋግ አይሉት ዳመና
ያዝ ለቀቅ የሚል ያለየለት
ምን ሊመስል ነው የቁርጡ ዕለት
ድብልቅልቅ ያለ አተላ
ገና በድፍድፉ የተበላ
የቆላ ማሩን በጋን ጥሎ
ብቅል ከጌሾ አስመጥኖ
አትረፍርፎ ስለአበላው
ጥጋቡ አልቻልህ ቢለው
ፊቱ ወርዝቶ ጉንጩን ሞላው
ያ ገበሬም እጀ ሰፊው
ምንም ተርፎት ሣያቀናው
በሬው ሙቶ ቢያከስረው
የልጅ ቀለቡን አናረው
ግራ ተጋብቶ መላ ቢያጣ
ለዘር ያስቀመጠውን አወጣ
አንድ ዕፍኝ ዘር ቢዘራው
የጎደለውን በቀን ሞላው
ቀን ያጎደለው በቀን ሲተካ
ያኔ ነው ልብ የሚረካ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፅንፈኛው የሕወሓት ቡድን የመሳሪያ አቅም እንዳለው የሚያስመስለው ሌላ አማራጭ ስላጣ ነው፦ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ|

Next Story

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና የጽንፈኛው ህወሃት ምላሽ

Go toTop