የካርታ ጨዋታ (ዘ-ጌርሣም)

November 16, 2020

የካርታ ጨዋታ አምና ተጀመረ
ጆከሩን በወለድ እያሰባጠረ
ሁሉንም በአንድ ዙር ሊልፈው ሞከረ
በአንድ ጊዜ ለመክበር ቁጭ ብሎ እያደረ
ብሩን በዶንያ ያግዘው ጀመረ

የካርታ ጨዋታ መዘዙ ብዙ ነው
መጀመሪያ ብሽቀት ሲቆይ መጫረስ ነው

ኑሮ አልሆንህ ቢለው የፈረንጅ አገሩ
የካርታ ሊቸንሳ ከፈተ በአገሩ

መበላቱን ሲያውቀው ምን ያስፐውዘዋል
ባይሆን የለመደው ገበጣው ይሻላል
የሚያከስብ መስሎት ቂልም ይሯሯጣል
ያጫዋቹን ተንኮል ማወቅ ተስኖታል

የካርታው ጨዋታ የአንድ ዓመት ስልጠና
በሚላኖው ምሩቅ በእሳቱ ተበላ
የሚላኖው ካርታ አገራችን ገብቶ
ሊያጣልዝ ተነስቷል ከፋፍሎ በጉቶ
ዋ ! መጨረሻው ይህ የካርታ ቁማር
ትዳርን አፍርሶ እንዳያደርግ እርር
ወልዶ ልጅ መተካት ሳለ ደጉ ነገር
ሳይሻል አይቀርም የጉግስ ጨዋታ
ለመግዛት ከሆነ ፈሪው እንዲረታ
የካርታው አጫዋች ሁሉን ይሞክራል
መች በዚህ አቁሞ በእምነትም ጀምሯል
የካርታው ጨዋታ እጅግ በመድራቱ
ሊበላው ወስኗል እስከ ቀለበቱ
አምና በጀመረው ከፍ ብሎ ከአንገቱ
ዘሃር የቆመለት መስሎ ስለታየው
የራሱን ጨምድዶ ለጎረቤት ናኘው
ነገ እሱ ሲበላ ከዚያ ላያገኘው
ሻጥር የበዛበት የካርታ ጨዋታው
ተሎ ካልተገታ መዘዙ ብዙ ነው
የአጫዋቹ ፊሽካ በአስቸኳይ ያስቁመው
የሚላኖ ካርታ ለጣሊያኖቹ ነው
ኢትዮጵያ ከገባ ዳግመኛ ቅሌት ነው
ይህን ያለጤነ ውርድ ለራሴ ነው
1991-05-30

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የመከላከያ ሠራዊቱ የጀመረውን ሃገርን ህልውና የማዳን ዘመቻ ዘራፊውን የህወሓት ቡድን ለህግ እስኪያቀርበው ድረስ እንደሚቀጥል ተገለፀ|

Next Story

ከሕዝብ እውነተኛ ፍላጎቶች መማር ብልኅነት ነው – አምባቸው ደጀኔ

Go toTop