በሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት መፈፀሙ ብዙዎችን እንዳሳዘነ ዜጎች በተለያየ መገናኛ ዘዴዎች የገለፁ ነዉ።”በማይካድራ የተፈፀመው ጭፍጨፋ አማራን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ሲል የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ድርጊቱን ኮንኖአል።
–የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን አስታወቀ። የትግራይ ክልል በበኩሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዉጃለሁ ማለቱ ተሰምቶአል።
–በትግራይ የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ በርካቶች ወደ ሱዳን ሊሸሹ ይችላል ተባለ። የዓለሙ የሰብዓዊ ጉዳዮች ድርጅት በክልሉ የሰብዓዊ ርዳታ በተቻለ ፍጥነት እንዲደርስ እንፈልጋለን ፤ ምግብ እና ነዳጅ በፍጥነት ሊደርስ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቦአል።
–በዩናይትድ ስቴትስ ረት በ 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 202 ሺህ ሰዎች በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተነገረ። በአንድ ቀን ብቻ 1535 ሰዎች በኮቪድ መሞታቸዉም ተዘግቦአል። አሜሪካ ከዓለማችን በኮሮና ወረርሽኝ የተጠቃች ቀዳሚዋ ሃገር ናት።
ዜናዉን በዝርዝር አዳምጡ !
DW