ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ (ዘ-ጌርሣም)

September 24, 2020

ማሳውን ዙሪያውን
ሜዳ ተራራውን
ቆፍረው ቆፋፍረው
ቀንበጡን ቦጥቡጠው
ዘሩንም አጥፍተው
ሌሊት ጩኸታቸው
ልፊያና ድሪያቸው
አላስተኛ እያሉ
አድረው እንዳልዋሉ
ጊዜው ደረሰና
ዘመን ተተካና
ምድሯ ተንቀጥቅጣ
ትራዋን ስትቀጣ
ሁሉም ተጠራርተው
ካዘጋጁት ቦታ ገቡ ጉድጓዳቸው
ኑሮውን ለመልመድ ምንም ቢቸገሩ
በቆፈሩት ግድጓድ በአንድ ላይ ታጎሩ
ዳግም ሳይዳሩ
በጠራራ ፀሃይ አንደውጡ ቀሩ
ለሁሉም ጊዜ አለው
ደረሰ ተራቸው
ጠቢቡ ሰለሞን እንደተናገረው
ጊዜው ባለ ጊዜ ሲቀየር አየነው
ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ
የሰበሰቡትን እንደሰለቀጡ
ሆድ የገባ ነገር አይቀርም መውጣቱ
መቆየት ተችሎ ከሰነባበቱ
ማሳው ለመለመ ተመቸው አትክልቱ
አይጦች ጉድጓድ ገብተው ቀሩ እንደታገቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አወዳደቅን ለማክፋት በነዚህ ነገሮች መበርታት! – ነፃነት ዘለቀ

Next Story

ሸገርና ምርጫ፣ ባልደራስና ፊርማ (አሁንገና ዓለማየሁ)

Go toTop