መታሰቢያነቱ ፦ በዓለም አቀፍ ሴራ ከቀዬአቸው ለሚሳደዱ የኢትዮጵያ ልጆች (አሁንገና ዓለማየሁ)

September 19, 2020

የመስተባርር ድግምቱ
ጉሙዝ አራጅ ሆኖ
አገው ታራጅ ቢሆን በገዛ መሬቱ
አሳራጁ ሰነድ ያ ሕገ መንግሥቱ
መለሰና ሌንጮ የጻፉት ሁለቱ
የውቅያኖስ ጆፌ እያያቸው ንሥር
በአቆርዳት በረሃ በኢሳያስ ጥላ ሥር።
….
ትግሬ አሳዳጅ ሆኖ
አማራ ቢሳደድ ከገዛ መሬቱ…
እስላም አራጅ ሆኖ
ክርስትያን ቢታረድ በገዛ መሬቱ…
ወንድሜ
መልሰው!
መላልሰው! አንድ ነው ድግምቱ
በሎንዶን ብራና የስታሊን ምትሐቱ
“አብርርልኝ! ልምጣ” ነው ሚሉት ቃላቱ።

መታሰቢያነቱ ፦ በዓለም አቀፍ ሴራ ከቀዬአቸው ለሚሳደዱ የኢትዮጵያ ልጆች

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ባዲሱ ዘመን ለሰው ልጅ ህይወት ክብር እንስጥ

Next Story

ሤራና ግድያ ሀሤራና ግድያ ሀገርን ያፈርሳል እንጂ አይገነባም! – አሣምነው ጽጌ

Go toTop