ሰላም ባይኖርም ሰላም ልበላችሁ ውድ አንባቢያን
ነገሩ የተፈጸመው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012ዓ.ም ነው፡፡ ጀሞ ሁለት በሚባለው አካባቢ አንዲት አነስተኛ ቡና ቤት ውስጥ የተከሰተ አስፀያፊ ድርጊት ነው፡፡ ባለቡና ቤቷ ለስምንት ዓመታት በሥራ ፍለጋ ያለምንም ሥራ ስትንከራተት ቆይታ አክስት አጎቶቿ ተባብረው አንዲት ቡና ቤት ይከፍቱላታል፡፡ በዚያ መተዳደር ከጀመረች ጥቂት ወራት አለፉ፡፡
ባለፈው ቅዳሜ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲህ ሆነ፡፡ የሠፈር ሰዎች በቡና ቤቷ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ይዝናናሉ፡፡ የሚናገሩት በአማርኛ ነው፡፡ በአጋጣሚ ደግሞ የተከፈተው ዘፈን ተራው ሆኖ አማርኛ ነው፤ ቡና ቤቶች ዘፈን እያፈራረቁ ነው የሚያዘፍኑት – በባለጊዜዎች/ተረኞች ካልተገደዱ በስተቀር፡፡ ያኔ ያካባቢው ቄሮዎች ይሰባሰቡና “ሆ!” እያሉ መጥተው “ናፍጠኞታ! ናፍጠኞታ!” በማለት ቡና ቤቱን በድንጋይ ሩምታ ያደበላልቁታል፡፡ እንዲህ ያደረጉት ሴትዮዋ አማራ መስላቸው ነው፡፡ እርሷ ግን በጊዜው አነጋገር ትግሬ ናት፡፡ በትግሬነቷ ግን አልተጠቀመችም እንደመረጃ ምንጬ፡፡
ዕብዶቹ በድንጋይ ቡና ቤቱን ማተረማመስ እንደጀመሩ ሴትዮዋ ደምበኞቿን ገፋፍታ በጓሮ በር አስወጣችና የሚሆነውን ለማየት ቤቷ ውስጥ በድንጋጤ ፈዝዛ ቁጭ አለች፡፡ እነዚያ ቄሮዎች በኦሮምኛ አማራን እየተሳደቡና እየተራገሙ ፍሪጁን፣ በርና መስኮቶችን፣ በቤት ውስጥና በግቢው ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ ሰባብረውና የዘረፉትንም ዘርፈው ወደመጡበት ተመለሱ፡፡ አንድም ገላጋይ አልነበረም፡፡ ሁሉም ለባለጊዜዎቹ ያጎበደደ ወይም በፍርሀት የራደ ነውና፡፡
ሴትዮዋ ህግ ያለ መስሏት ልታመለክት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደች፡፡ እንደሄደች ላገኘችው ፖሊስ የደረሰባትን ግፍና በደል ስትነግረው በነገር ጥልልፍ ትግሬ መሆኗን ያወቀው ፖሊስ በተሰባበረ አማርኛ “አንቺ ወያኔ ነሽ ኢንዴ… ነፍጠኛ አይደላሽ ኢንዴ… ነፍጣኛ ናትኮ ነው ያሉት ልጆቹ፡፡ ላናጋሩ ሁለታቹም አንዲ ናቹ…ምንም ሊናራግ አኒችልም…” በማለት አሹፎባትና ስቆባት አመናቅሮ እንደመለሳት የመረጃየ ምንጭ በምሬት ገልጾልኛል (እዚህ ላይ የፖሊሱን ንግግር እንደሰማሁት እንዳለ ለማስቀመጥ እንጅ ስለቋንቋ ችሎታው ለመተቸት አይደለም፤ ቋንቋን መቻል አለመቻል ምንም ማለት አይደለም፡፡ ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ እንጅ የማንነት መገለጫ እንዳልሆነም አሳምሬ እረዳለሁና በሌላ መልክ እንዳትመለከቱብኝ አደራችሁን፡፡ መጥፎው ነገር የኔ የሚሉትን ግን የሁሉም እንጅ የማንም ያልሆነን አንድ ቋንቋ ካልተናገራችሁ ብሎ ልክ እንደ አዲሶቹ ወያኔ/ኦህዲድ/ኦነጎች ‹አገር ይያዝልን!› ብሎ መሞላፈጥና አገርን ለማፍረስ ባለ በሌለ ኃይል መራወጥ ነው፡፡ እንጂ አንድ ኢትዮጵያዊ አማርኛ ባይችልም – ቢችል ጥቅሙ ለራሱ ሆኖ – በራሱ ቋንቋና በትርጁማን አገርን በፍትህ ርትዕ ማስተዳደር የዜግነት መብቱ ነው፡፡ ሌሎች ዘውጎችንም አለመርሳት ይገባል ደግሞ! የወያኔና ኦነግ አንደኛው ትልቅ ችግር ከዚህም ይመነጫልና)፡፡ ይህ መረጃ በነገራችን ላይ የአካባቢው የቡና ማጣጫ ነው – ሁሉም የሚያውቀው፡፡ በዚህ ሁኔታ አክራሪ ኦሮሞ ሀገራችንን እንዴት እያመሰቃቀላት እንደሆነ ከዚህ አሳዛኝ ድርጊት መረዳት ይቻላል፡፡ ከሚዘገበው ደግሞ የማይዘገበው እጅግ ይበዛል፡፡ አዲስ አበባ እንጃላት! ታስፈራለች፡፡
ይህች ናት ኢትዮጵያ፡፡ ነገሮች በብርሃን ፍጥነት እየተበለሻሹ ነው፡፡ የትናንትናው የነመረራ የትዳር አፍርሱ ጉዳይ ደግሞ እጅግ የሚገርም ነው፡፡ “አማራን ፈትታችሁ እኔን አግቡኝ” የምትል ጉድ እንደተፈጠረች በግልጽ እያየናት ነው፡፡ ይህ ሀፍረት የሚሉት ነገር ከሀገር ተሰድዶ ጠፍቷል፡፡ የሚታየውና የሚሰማው ሁሉ እጅግ ያስጨንቃል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡