የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የምስረታ ጉባኤ በመኢአድ የጽህፈት ቤት ሲያካሂድ መልዕክት እንዲያስተላልፍ ተጋብዞ ካስተላለፈው መልዕክት በከፊል
_ ሁላችንም በጋራ ለሀገራችን መስራት አለብን
_ ምርጫ ይደረጋል ተብሏል ህዝቡ ስለሚመርጠው ድርጅት ማወቅ አለበት
_ የመረጭነት ካርድ ወስዶ መብቱን ጥቅሙን ሊያስጠብቅለት ለሚችለው ድርጅት መስጠት አለበት _ይህንን ሳያደርግ መብቴ ተነካ ተባረርኩ እያለ ማማረር ተገቢ አይደለም ጥፋቱ የራሱ የህዝቡ ይሆናል
_ በኛ በኩልም ጠንክረን በመስራት ለአሸናፊነት መዘጋጀት አለብን
_ እንደከዚህ በፊቱ ተሸናፊውን አጅበን የቤተመንግሥት የምናስገባበት አሸናፊው ወደ ከርቼሌ የሚገባበት መንገድ መቆም አለበት ።
_ ምርጫው እንደከዚህ በፊቱ የሚሆን ከሆነ ህዝቡ ለቀጣይ ትግል መዘጋጀት አለበት ብሏል ።