አብመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ
•“ እስካሁን ድረስ በእገታው ምክንያት ጥቃት ደርሶ አንድም ሰው ስለመሞቱ ሪፖርት አልተደረገም፡፡”
•“ በአንድ ሀገር ሁለት የታጠቀና ሁለት መንግሥት ሊኖር አይችልም፡፡” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር)
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡ ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄና አስተያዬቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሰጡ ማብራሪዎች መካከል፡-
•ደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ እገታ በተመለከተ እገታውን “ኃላፊነት እወስዳለሁ” የሚል አካል ባለመኖሩ ችግሩን ውስብስብ አድርጎታል፡፡
• እስካሁን ድረስ መከላከያ በአካባቢው እያደረገ ባለው ጠንካራ ክትትል አንድም የተጎዳ አካል አልተገኘም፡፡
•ጉዳዩ ውስብስብ በመሆኑ በጥንቃቄ እየተሠራበት ነው፡፡
•እስካሁን ድረስ በእገታው ምክንያት ጥቃት ደርሶ አንድም ሰው ስለመሞቱ ሪፖርት አልተደረገም፡፡
•መንግሥት መግለጫ ለመስጠት የዘገየው በምክንያት ነው፤ መንግሥት ባልተሟላ መረጃ መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት አጋቾች በታጋቾች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመጠንቀቅ ነው ፈጥኖ መግለጫ ያልተሰጠው፡፡
•የችግሩ ተጠቂ ወላድ ብቻ ሳትሆን ሠላም ወዳድ ሕዝብና ሀገር ነው፡፡
•ጉዳዩን በሚመለከት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በሰላም ሚኒስቴር የሚመራው ግብረ ሃይል የተደራጀ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡
•በአንድ ሀገር ሁለት የታጠቀና ሁለት መንግሥት ሊኖር አይችልም፡፡
•ወንድም ወንድሙን መግደል አያኩራራም፤ ሰው ሀሳቡን በንግግር፣ በድርድር፣ በውይይት ቢጨርስ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ሁለት መንግሥት ያለው ሀገር እንዳይሆን ህጋዊ መንግሥት ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል፡፡
•ያለንበት ወቅት ፈታኝ፣ የመጨረሻ የሞት ሽረት፤ ነገር ግን አሸንፈን ብልጽግናችን የምናረጋግጥበት መድረክ በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተከበረው የምክር ቤት አባላት ከዚህ አንጻር ድጋፍ ማድረግ ከሁላችሁም የሚጠበቅ ይሆናል፡፡”