የምታዩት ቪዲዮ የጋራ የሆነ የሚያግባባ ቅርጸ መንግስት ይሆናል ተብሎ የቀረበ ቅርጸ መንግስት ነው። በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ ሃገራችን የፌደራል ስርዓት ተከታይ እንድትሆን ሰፊ መግባባት ቢኖርም ነገር ግን የፌደራል ስርዓቱ ምን መምሰል አለበት በሚለው ላይ ሰፊ ልዩነት አለ። ሃገራችን በዚህ የሰፋ ቅርጸ መንግስት ልዩነት ረጅም ጊዜ ልትቆይ አትችልም። በቅርጸ መንግስታችን ላይ መግባባት ለጠራ መድብለ ፓርቲ ስርዓት እና መረጋጋት ወሳኝ ነው። የዚህ የጣምራ ፌደራሊዝም እሳቤ ከየአቅጣጫው ያሉ እውነቶችን በማገጣጠም የተሰራ ነው። ይህንን እሳቤ ተመልክተነው እንደ አማራጭ ሃስብ አይተነው እንወያይበት::
https://youtu.be/K8EYCSzXwoc