በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው ተባለ

November 24, 2013
የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የ3ኛ ዓመት የዲግሪ ተማሪ የሆነው ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በፅንፈኛው ወያኔ አባላት በጩቤ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ሟች ወጣቱ ያነሳቸው የነበሩ ጥያቄወች በስፋት መነሳት ጀምረዋል ሲል  የ አማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን)  ለዘ-ሐበሽ በላከው መረጃ አስታወቀ።

“ሟች አንተነህ ዘረኛው የወያኔ ወራሪ ቡድን በንፁሃን አማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ዉስጥ አየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለፍርሃት ይቃወም የነበረ ሲሆን ደካማው የወያኔ ቡድን የለመደውን ደም ማፍሰስ ተግባሩን ፈፅሞበታል” ያለው  አወጋን  “ወጣቱ የተገደለው በጩቤ ተወግቶ ሲሆን እሬሳው ከዳሽን ብራ ፋብሪካ በስተጀርባ ተጥሎ ተገኝቷል” ሲል ዘግቧል።(

“የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ እሄን አስከፊ የሆነ የጠባቦች ድርጊት አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን ወነጀለኞችን በተገኙበት ለመቅጣት ያለ እረፍት ይሰራል ወጣቱ ከዚህ መማር ያለበት ነገር ቢኖር የወንድማቺን የአንተነህ እጣ ሳይደርሰው ወያኔን ለማስወገድ የምናደርገውን ትግል በመቀላቀል የወገኖቻችን የስቃይ አመታት እናሳጥር በማለት መልክቱን ያስተላልፋል” ያለው አወጋን “ለሟች ቤተሰቦች መጥናናቱን ይስጥ” ሲል ሐዘኑን ገልጧል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አሁንም ውጥረቱ እንዳየለ ነው ቢባልም የመንግስት ሚድያዎች አንዳችም መረጃ አልሰጡም።

Previous Story

ይድረስ ለሀይለማርያም ደሳለኝ – መልዕክት በግጥም

Next Story

Hiber Radio: በሳዑዲ ትላንት ሁለት ኢትዮጵያውያን ተረጋግጠው ሞተዋል

Go toTop