በጀነራል ደግፌ በዲ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ እሁድ የካቲት 17/2011 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ሠላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰተኛ ነው ሲል መግለጫ ሰጠ::
https://youtu.be/9_PNwyW18Qg
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል ጥያቄ አልቀረበልኝም ያለው” ኮሚሽኑ ሰልፉ የሚደረግ ከሆነ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው ብሏል::
“ሰልፍ እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል:: ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ ርምጃ እወስዳለ” የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል::
ባለፈው መስከረም በቡራዩ የደረሰውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ በወጣበት ወቅት መከላከያው 6 ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደሉ የሚታወስ ነው::
በሌላ ዜና በጎንደር ደባርቅ ከተማ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና እንደማይሰጥ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ። 4ኛው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዲራዘም ለመጠየቅ የተጠራው ሰልፍ በነገው ዕለት እንደሚደረግ አዘጋጅ የሰ/ጎንደር ዞን አማራ ወጣቶች ህብረት አስታውቆ ነበር::