የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኘውን የሁመራ ኦምሃጀር መንገድ ዘጋ

February 23, 2019

በሁመራ ኦምሀጁር በኩል ያለው የንግድ እንቅስቃሴ መዘጋቱ ተነገረ፡፡ ኤርትሪያን ፕሬስ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው መንገዱን በአጣና የዘጋው የትግይ ክልል መንግስት ነው፡፡ ይህ የሁመራና ኦምሀጁር መንገድ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚያገናኝ ዋናው መስመር እንደሆነ ይታወቃል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=9_PNwyW18Qg&lc=z232dvlz4rjojzig504t1aokggiygcg51eftmpfbzcukrk0h00410

በሁመራ ያሉ አንድ ምንጭ ለኤርትሪያን ፕሬስ እንደተናገሩት በዚያ መንገድ ሲጓዙ ከነበሩትና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችንና ጤፍ ጭነው የነበሩትን ከባድ መኪናዎች በማስቆም ትግርኛ ተናጋሪ ካልሆኑት በተለይ ከኦሮሞና አማራ ተወላጅ የተባሉት ላይ እየተመረጡ ላይ ዘረፋ ፈፅመዋል፡

ይህ ድርጊት የተፈፀመውም የክልሉ መንግስት ዋና መቀመጫ ከሆነው መቀሌ በተላለፈ የከፍተኛ ባለስልጣናት ትእዛዝ መሆኑን የዜና ምንጩ አስረድቷል፡፡

ይህ በሁመራ ወደ ኦምሀጁር የሚወስደው መንገድ ለ20 አመታት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ የተከፈው በቅርቡ ሁለቱ አገራት ከታረቁ ወዲህ መሆኑ ይታወቃል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=9_PNwyW18Qg&lc=z232dvlz4rjojzig504t1aokggiygcg51eftmpfbzcukrk0h00410

Previous Story

አዲሱ አረጋ ከለገጣፎ መልስ የጻፉት ጽሁፍ

Next Story

የአዲስ አበባ ፖሊስ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ስለመጠራቱ ጥያቄ ያቀረበልኝ አካል የለም አለ

Go toTop