“በመሃልና በምዕራብ ጎንደር በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ሲዘገብ ሰንብቷል። ቀውሱ በመተማና አካባቢው ሲጀምር መንግሥት ፈጥኖ እርምጃ ባለመውሰዱ ልዩ ልዩ አጀንዳ ያላቸው ታጣቂ ሃይሎች ሁኔታውን በመጠቀም ቀውሱ እንዲባባስ ለማድረግ እድል አግኝተዋል።
https://www.youtube.com/watch?v=9K1EwuewSOA
በዚህም ምክንያት ከመተማ እስከ ጎንደር እና ከጎንደር እስከ ትክል ደንጋይ ከዚያም አልፎ ወደ ሁመራ በሚወስደው መንገድ ሁሉ ችግሩ እንዲባባስ ሆኗል። በዚህም ምክንያት ከ 50000 እስክ 60000 የሚሆኑ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። በአሁኑ ወቅት በትክል ደንጋይ፣ በአይምባ፣ በወለቃ፣ በመተማ አካባቢና በሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ሲሆን፤ ወደ ሱዳን የገቡ ተፈናቃዮችም እንዳሉ ይነገራል።” ሲል መግለጫ ያወጣው ጎንደር ሕብረት “የጎንደር ሕብረት በደረሱት ዘገባዎች ላይ ተመስርቶ ለተፈናቃዮች እርዳታ ለማድረስ አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር (1,000,000.00) መድቧል።
እርዳታውም በአስቸኳይ እንዲደርስ ጎንደር ላለው ቅርንጫፍ መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ መሬት ላይ ባለው ዘገባ ላይ ተመስርቶ እንደሁኔታው የእርዳታውን መጠንም ከፍ ለማደርግ ወስኗል። አባላቱ፣ ደጋፊዎች እና መላ ማህበረሰቡ የወገኖቻችንን ሰቆቃ ለመቀረፍ በሚደረገው ጥረት በስቴት ቅርንጫፎች በኩል ገንዘብ በማሰባሰብ የበኩላቸውን አስተዋጽዎ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።” ብሏል::
–