በትግራይ ክልል ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የአስተዳደር አደረጃጀት መዋቅር ለመቀየር የሚያስችል ሪፎርም እየተካሄደ መሆኑን ዶ/ር ደብረጺዮን ገለጹ:: የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 14 ተኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በመቐለ ሲጀመር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የክልሉን መንግስት የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s
ዶክተር ደብረጽዮን ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት የክልሉ ተወላጆች ከተለያዩ አካባቢዎች የመፈናቀል ሁኔታ አሁን ድረስ መቀጠሉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠር በክልሉ ያለውን ሰላም ለማደፍረስ ሲከናወኑ የነበሩ እንቅስቃሴዎችን የክልሉ ህዝብና የፀጥታ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ስራ ማምከን መቻሉን አንስተዋል። የህግ የበላይነትን ለማስከበር ባለፉት ስድስት ወራት የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም በሌሎች አካባቢዎችን ተቀባይነት አግኘተው ውጤታማ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የአስተዳደር አደረጃጀት መዋቅር ለመቀየር የሚያስችል ሪፎርም እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ደብረጺዮን በዚህም በክልሉ ያለውን መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ የሚያስችል በገጠር ቀበሌዎች የነበረውን የመሬት ዳኝነት ኮሚቴ እንዲፈርስ መደረጉን;በገጠር ጣቢያዎች የነበረው የካቢኔ ቁጥር ከ 15 ወደ 3 እንዲቀነስ መደረጉን; በአጠቃላይ በከተማና በገጠር ቀበሌዎች ያሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል በጥናት የተደገፈ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
እንደ ዶክተር ደብረጽዮን ገለፃ በክልሉ የሚፈፀሙ የመንግስት ስራዎች በሙሉ በጥናናት ፣ በምርምርና በቴክኖሎጂ ተደግፈው የሚከናወኑ ይሆናሉ:: ባለፉት ስድስት ወራት ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ ታልሞ በተሰራው ስራም ከክልሉ የተለያዩ ህብተረሰብ ክፍሎች በክልሉ በሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት 583 ሚሊየን ብር ተቀማጭ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ባለፈም በክልል ለሚገኙ 867 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን አብራርተዋል::