ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ…

January 24, 2019

ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹ ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ በኃላ ወደ ጎንደር እየተመለሱ ጣራ ገዳም በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ነው የመኪና አደጋው ያጋጠማቸው።

በአደጋውም የሁለት ደጋፊዎች ህይወት ሲያልፍ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ደጋፊዎች ላይም የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በተሽከርካሪ አደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በጎንደር ሆስፒታል እና በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አስታውቋል።

Previous Story

በትግራይ ክልል ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የአስተዳደር አደረጃጀት መዋቅር ለመቀየር የሚያስችል ሪፎርም እየተካሄደ መሆኑን ዶ/ር ደብረጺዮን ገለጹ

Next Story

አቶ በረከት ስምኦን በነጠላ ጫማ ፍርድ ቤት ቀረቡ! 

Go toTop