የአንጋፋው የኦሮሞ አርቲስቶች ባንድ አርፈን ቀሎ አባላት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

January 19, 2019

የአንጋፋው የኦሮሞ አርቲስቶች ባንድ አርፈን ቀሎ አባላት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

https://www.youtube.com/watch?v=I4V8VygwOuk&t=204s

ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የባንዱ አባላት 17 ሲሆኑ፥ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና በአድናቂዎቻቸው አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የባንዱ አባላት ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ ህዝቡ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት እንዲፈጥር የበኩላቸውን ሲያበረክቱ መቆየታቸው ተዘግቧል;; ዛሬ  ኢትዮጵያ የገቡት የባንዱ አባላት በአርቲስት አሊ ሸቦ፣ አርቲስት ቱሬ ሌንጮ፣ አርቲስት ሸንተም ሹቢሳ፣ አርቲስት ጃፋር አሊ፣ አርቲስት አደም ሀሩን እና ፕሮፌሰር ጀማል ሀሰን መመራታቸው ሲገለጽ  ወደ ሀገር ቤት የተመለሱትን አርቲስቶች ጨምሮ አዳዲስና ነባር የኦሮሞ አርቲስቶችን የሚያሳትፍ የሙዚቃና የጥበብ ኮንሰርት ለጥር 18 ቀን 2011 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይደረጋል ተብሏል::

 

Previous Story

የአሜሪካ እርዳታ በግማሽ ሊቀንስ ነው

Next Story

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ..

Go toTop