የኦነግ ጦር የደቡብ ዞን አዛዥ የሰላም ጥሪውን ተቀበለ

January 16, 2019

በኦነግ ጦር የደቡብ ዞን አዛዥ የሆነው ኤሊያስ ጋምቤላ ጎሎ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀበለ፡፡ በትላንትናው እለትም ወደሰላማዊ ትግል ተመልሶ ወደተዘጋጀለት ማረፊያ ገብቷል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=epx_GOJUaUQ

የሰላም ጥሪውን ያቀረቡት የጉጂ አባ ገዳዎች ሲሆኑ ጥሪውን ተቀብለው ሌሎች የኦነግ ሸኔ አመራሮች እየተመለሱ መሆኑም ታውቋል፡፡ የጉጂ አባ ገዳ ጂሎ መንኦ ዛሬ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ‹‹በጉጂ እና ምእራብ ጉጂ ዞን በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጦር አመራሮች የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደተዘጋጀላቸው ማረፊያዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ።› ብለዋል፡፡ አባ ገዳዎች ከመንግስት ጋር በነበራቸው ውይይት በተስማሙት መሰረት የዞኑ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጦር ወደተዘጋጀላቸው አራት ካምፖች እየገቡ መሆኑን የጠቆሙት ጂሎ መንአ በመንግስት በኩል ያለውን ቀሪ ጉዳይም የአባ ገዳዎች ከመንግስት ጋር በመመካከር እንደሚጨርሱ አስረድተዋል፡፡ የጉጂ አባ ገዳዎች ባሳለፍነው ሳምንት አውጀውት የነበረው የሰላም ሳምንት በዚህኛው ሳምንትም እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን ከሰላማዊ ትግል ውጪ የሚደረግ ማንኛውንም የትጥቅ ትግል ተቀባይነት እንደሌለው አባ ገዳዎቹ ገልፀዋል፡፡

Previous Story

የክፍለ ከተማው ባለስልጣን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ ይዘው ተሰወሩ

Next Story

አዲስ አበባ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጠለሉ ተፈናቃዮች ግቢውን እንዲለቁ ተጠየቁ

Go toTop