በትናንትናው እለት አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ በርካታ ምእመናን ተቃውሞዋቸውን አሰምተው ተመልሰዋል፡፡ የተቃውሞው መነሻም ቀሲስ መላክ ሩፋኤል የማነ ናቸው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
አባ ሩፋእል ሰው ቀደም ሲል ሲኤም ሲ አካባቢ በሚገኘው የሳአሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆን በደብሩ ላይ በፈፀሙት ከባድ የአስተዳደር በደልና የገንዘብ ችግር ምእመናን ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል እንዲነሱ ተደርገው ነበር፡፡
ይሁንና ከሳሊተ ምህረት ከተነሱ በኋላ ወደ የካ ሚካኤል ተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ተመድበው ነበር፡፡ የየካ ሚካኤል ምእመናንም ባደረጉት ትግል ሰውየው እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ አሁን ደግሞ ግለሰቡ በቦሌ ደ/ምህረት ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብባቤ ይዘው ወደቤተክርስቲያኑ ሄደዋል፡፡ ይህን በመቃወም ትናንት የቦሌ ሚካኤል ደብር የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በመንበረ ፓትሪያርኩ ተገኝተው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፡፡
ጥያቄያቸውን ለፓትሪያርኩ ለማቅረብ ቢፈልጉም የመንበረ ፓትሪያርኩ ጥበቃ አባላት በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት በሩን ዘግተውባቸዋል፡፡ በዚህ ቤተክርስቲያን ቀደም ሲል የነበሩት አስተዳዳሪ መላከ ጸሀይ ስዪም ወ/ገብርኤል የተነሱት በአስተዳደራዊ ችግር ነበር፡፡ ምእመናኑ የያዙት መፈክርም ይህን ለመግለፅ ነው መባሉን ሰምተናል::