የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት ባለሥልጣን ካሳቫ የተባለው ሥር በእንጀራ መልክ እንዲቀርብ መፈቀዱን ለጣቢያችን አስታውቋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ካሳቫ የተባለው ሥር ከምግብ ምድብ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ከእንጀራ ምርት ጋር ተቀላቅሎ ለምግብነት እንዲቀርብም በደረጃዎች ሲፈቀድ እኛ ደግሞ የመቆጣጠር ስራውን እንሰራለን ብለዋል።
ይህንን ተገን በማድረግ ሌላ ባዕድ ነገር እንዳይቀላቀል የቁጥጥር ሥራ ይሠራል ብለዋል።
አሁን ላይ ምርቱ ከክልሎች በመምጣት አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በስፋት እንደሚገኝም ተነስቷል፡፡
የካሳቫ ተክል ከፍተኛ የካርቦሀይድሬት መጠን ያለው ሲሆን በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ምግብ መሆኑንንም በጥናት ማረጋገጣቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።
ካሳቫ የስኳር በሽታን፣የልብ በሽታን እንዲሁም የህዋስ እርጅናን/cell aging/ እንደሚከላከል ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ።
ካሳቫ የስራስር አይነት ሲሆን፤ በተለይ በደቡብ የሀገሪቱ ከፍል በወላይታ እንዲሁም በጋሞ ዞን ምርቱ በብዛት እንደሚኝም የባለስልጣኑ ዋና ሃላፊ ጨምረው ገልጸዋል።
#
የዜናው ዘገባ የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው