የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 10, 2025 ነፃ አስተያየቶች Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡ 3 የአማራ የህልወና ትግል የአማራ ታጋዮች የጋራ ግንዛቤ፤ የአማራ የህልወና አደጋ እንዲህ በቀላሉ በዋዛ ፈዛዛ የሚቃለል እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። አማራን ስትራተጂያዊ ጠላታቸው አድረገው የሚያዩ አለምአቀፍ፣ ቀጠናዊና ሃገራዊ አካላት አሉ። እነዚህ አካላት ከፍተኛ ሃብት ወታደራዊ ጉልበት፣ ስነልቦናዊ ዝግጅት አላቸው። የአማራ ህዝብ ትግል ይመለከተኛል የሚል ማንኛውም አካል እነዚህ አካላት እነማናቸው የሚለውን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል። ማወቅ ማለት ግን በሚድያ የመናገር ወይም ጽሁፍ ጽፎ ማሰራጨት የሚችልበት አጋጣሚ በተፈጠረ ቁጥር ነጋ ጠባ የአማራ ጠላቶች እነዚህ ናቸው እያሉ ማንቧረቅ ማለት አይደለም። አሁን የአማራ ህዝብ የሚገኝበትን የህልወና አደጋና የመከላከል አቅሙ ደረጃ በቅድሚያ አንድና አንድ ነገር ላይ ብቻ እንዲያተኩር ያስገድደዋል። የሃገሪቱን ታንክና ባንክ ተቆጣጥሮ በአማራ ህዝብ ላይ ከዚህ ዘመን በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የዘር ፍጅት እያደረሰበት ካለው የአብይ አህመድ አገዛዝ በላይ አማራ ጠላት የለውም። ከዚህ ጸረ አማራ አገዛዝ ጋር ለሆዳቸው አድረው በተላላኪነት ከሚያገለግሉ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትና የአብይ አደግዳጊ ባንዳ ምሁራን በላይ ጠላት የለውም። በትግል ወቅት የጠላትነትም ሆነ የወዳጅነት ደረጃዎች መታወቅ አለባቸው። ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ እንደማይወጣ ሁሉ የተወሰነ ሰራዊት አለኝ ተብሎ ከዋናው ጠላት እኩል ሊወዳደሩ ከማይችሉ፣ ጉልበት ሲደረጅ ልዩነትን በውይይት ወይም በድርድር መፍታት ከሚችሉ መለስተኛና አነስተኛ ጠላቶች ጋር ሁሉ “ኑ ግጠሙኝ” የሚል መልእክት ማስተላለፍ አደገኛ እንደሆነ መታወቅ አለበት። አማራው የራሱን የቤት ስራ ሳይሰራ፣ እራሱን ከህልውና አደጋ መከላከል የሚያስችል ጥርት ያለ ሁሉንም አማራ የሚገዛ ርእዮተአለምና ማንም ጉልበተኛ አደብ ማስገዛት የሚያስችል አንድ ወጥ ወታደራዊ ቁመና ሳይላበስ በቀጥታ ከህልውናው ትግል ጋር ግኙነት በሌላቸው የሃገራት፣ የቀጠናው የአፍሪካና የአለም ጉዳዮች ላይ የሚጨነቅብት ምንም አይነት አመክንዮ ማቅረብ አይቻልም። አማራው በኢትዮጵያ በቀጠናው በአለም ጉዳዮች ላይ መሳተፍ የሚችለው ህልወናው ማረጋገጥ የሚያስትል ዋስትና በጁ ሲገባ ነው። አሁን አማራው ያለበት ሁኔታ ይህን ዋስትና ከማግኘት እጅግ የራቀ ነው። የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ጥንካሬውን እድገቱን ግምት ውስጥ ያላስገባ ፋይዳቢስ ከሆነ የትኛውም ግዜን ጉልበትን እውቀትን አባካኝ ከሆነ ማንኛውም አይነት የሃገር ውስጥ ተሳትፎ መታቀብ ይኖርበታል። አማራ ይህን የሚያደረግው፣ እንደሌሎች የሃገራችን አክራሪ ብሄረተኞች በጥላቻ ላይ የተገነባ፣ ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰቦችን መቅረብ ሰለማይፈልግ ወይም ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ብትንትኗ ቢወጣ ደንታ ስለሌለው አይደለም። ከሃገረ ኢትዮጵያ ጋር ጠብ ስላለው እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። ይህን ሃቅ እያወቁ አማራ “ዝንጀሮ መጀመሪያ መቀመጫየን አለች” በሚል ትክክለኛ ብሂል በመመራት፣ እንደ ህዝብ ሊያጠፋው የመጣውን ማንኛውን ጸረ አማራ ሃይል መመከት የቅድሚያ ተግባሩ ስላደረገ፣ አማራ ስለሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድምና እህቶቹ ደንታ እንደሌለው፣ እንደሌሎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚነቀሳቅስ አድርገው ለሚስሉት የትኞቹም አካላት ምላሽ በመስጠት ጊዜውን ማጥፋት፣ በተከላካይነት ስሜት መቆም የለበትም። ይህን አስተያየት በአማራው ላይ መሰንዘር የጀመሩት በምንጅላት ታሪካቸው የባንዳ እዳ ያለባቸው ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች መሆናቸው መገንዝብ ተገቢ ነው። አማራ ማንነቱን የሚያውቅ በራሱ የሚተማመን በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ የትኞቹም ማህበረሰቦች ሆነ ለኢትዮጵያ ጥላቻ የሌለው ስልጡን ህዝብ ነው። ጽንፈኛ ብሄረተኞች ዘመናትን ያስቆጠረ በህግ በባንክና በታንክ ያሰራጩት የአማራ ጥላቻ በተዘራባት ኢትዮጵያ፣ ዛሬ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች የአማራ የህልውና ተጋድሎ መሳካት፣ የእነሱ ህልወና ዋስትና እንደሆነ የተረዱበት ሰአት ላይ መድረሳቸውን አማራው ተገንዝቧል። ይህ ሃቅ አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ የሚያደርገውን ትግል ለማንኳሰስ ለሚፈልጉ የአማራ ሆነ የሌሎች ብሄረሰብ ልሂቃን፣ የአማራ ታጋዮች መልስ መስጠት የሌለባቸው እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ ነው። “ሙያ በልብ ነው” እዚህ ላይ ይሰራል። አማራ እራሱን ሳያድን ኢትዮጵያ እንደማትድን አውቆ ያለምንም መሳቀቅ በሙሉ ልባምነት እራሱን ለማዳን ማድረግ የሚገባውን ሁሉ ማድረግ ይገባዋል። አለም የሚያውቀው ሃቅ አማራ ላይ ለዘመናት ተጠናክሮ የቀጠለው የጥላቻ ትርክትና የማያቋርጥ ጥቃት ምክንያቱ አማራ ሌላ ወንጀል ኖሮበት አይደለም። ኢትዮጵያን እንደሃገር ለማስቀጠል በከፈለው ወሳኝ መስዋእትነት፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እቅድ የነበራቸውን የውስጥና የወጭ ጠላቶች ህልም በማምከኑ ነው። የአማራው ህልውና የሚከበርበት ሁኔታ ከመጣ በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበው የህልውና አደጋ የሚያበቃለት መሆኑን መጠራጠር አያስፈልግም። ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ዛሬ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት ትልቅ ምስቅልቅል ዋናው ምክንያት፣ ከዚህ ምስቅልቅል በዋንኛነት ሊታደጋት ይችል የነበረው የአማራ ህዝብና ልሂቅ፣ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ሃይሎች በሰሩት የሚያስገርም የፖለቲካ ስርጀሪ በሃገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ህይወት ውስጥ ሚና እንዳይኖረው መድረጉ ነው። ሁለንተናዊ አቅሙ እንዲቀጭጭ የተሴረበት በመሆኑ ነው። በዚህ ልዩ የፖለቲካ ቀዶ ጥገና አማራው፣ እንኳን ለሃገር ለራሱም መቆም እንዳይችል ማድረጋቸው ነው። ትልቁ ጥያቄ እንደህዝብ እንዲቀጭጭ የተደረገ ህዝብ፣ እንደህዝብ ወደ ትንሳኤ የሚወስደው ትክክለኛና ፈጣን መንገድ የትኛው እንደሆነ መለየት ነው። እውን ይህ መንገድ ዘረኞች ባንክና ታንኩን ተቆጣጥረው ባለፉት 35 አመታት ለሃገራዊ የፖለቲካ አደረጃጀትና እንቅስቃሴ ግጥም አድርገው የዘጉትን የፖለቲካ ምህዳር እንዳልተዘጋ እያስመስሉ፣ ዛሬም እርባና የሌላቸውን ሃገራዊ ፓርቲዎች እናጠናክር ወይም እንደ አዲስ እንፍጠር የሚል ጥሪ ማድመጥ ነው? እስከዛሬ ሲደርግ እንደነበረው በስም ኢትዮጵያዊ በአባላት ይዘታቸው በአማራ የተሞሉ ድርጅቶች እየፈጠሩ፣ በየትኛውም ክልል እንደልብ ተንቀሳቅሶ አባል መመልመል ቢሮ መክፈት በማይቻልበት ሁኔታ መባዘን ነው መፍትሄው? ይህ አካሄድ ከወያኔ ዘመን ጀመሮ በአማራ ህዝብ ላይ የተፈጸምው ግፍ ማስቆም ያልቻለ አካሄድ ነው። ከወያኔ ከልስጣን መገለል በኋላ በመጣውና ከወያኔ ዘመን የባሰውን እጅግ አሰቃቂ የአማራ ህዝብ ፍጅት መፈናቀል፣ በገፍ መታሰር መዋረድ ማስቀረት ያልቻለ ነው። ዛሬስ የአማራ ህጻናትና አረጋውያንን በድሮን እንዳይጨፈጨፉ ማድረግ ችሏል ወይ? እነዚህ ሃገራዊ ድርጅቶች መግለጫ ከማውጣት አልፈው ለአማራው ምን ፈየዱ፣ እንደ ኢዜማ አይነቶቹ በአማራ ህዝብ ደምና አጥንት ላይ ህልውናቸውን የመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ከአብይ አገዛዝ ጋር ተደምረው አማራን የሚጨፈጭፍ ህግ አብይ ሲያወጣ የድጋፍ ድምጻቸውን አልሰጡም? ዘመኑ የሚጠይቀው አካሄድ ማንኛውም አማራ በተለይ እንደ ኢዜማ ከመሰሉ በአማራ እልቂት ከኦሮሞ ብልጽግና እኩል ተጠያቂ የሆኑ መሪዎች ካሉት ድርጅት መልቀቅ፣ የአማራን ትግል በአማራነቱ ተቀላቅሎ ማገዝ ነው። በሌሎችም ሃገራዊ ድርጅቶች ውስጥ የሚንቀሳቅሱ አማሮች “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” የሚለውን የአማራ ተረት ልብ ሊሉ ይገባል። ስልፋቸውን ከአማራው የህልውና ትግል ጋር ማሳመር ብቻ ነው የሃገራዊ ፖለቲካ ህልማቸውን ማሳካት የሚችሉት። በኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ዜጋ እንዳሸው እንዳይደራጅ፣ በዘረኞች የተዘጋውን የፖለቲካ ምህዳር መከፈት የሚችለው፣ አማራው የህልውናውን አደጋ ለመቀልበስ በሚያደርገው ትግል ብቻ ነው። ሌላ አማራጭ የለም። የዚህ ትግል አደረጃጅት፣ ለመንቃት፣ ለመደራጀት ለመታጠቅ ምቹና ፈጣን እድል የሚሰጠው አማራዊ አደረጃጀት ብቻ ነው። ፖለቲካ የሚሆኑ ነገሮች ጥበብ ነው የሚባለውን ከብዙ የፖለቲካ ተመክሮች ላይ ተመስርቶ የተቀመረውን አባባል የሚረዳ ማንኛውም አማራ፣ ትክክለኛው አማራጭ በአማራነት መደራጀት እንደሆነ ሊስተው አይገባም። ይህ ሃቅ ነው የአማራን የህልውና ትግል ሃገር አፍራሽ፣ ዘረኝነትን አባባሸ አድረግው የሚያዩ አካላት ከተሳሳተ አመለካከታቸው ታርመው፣ አማራ ለህልውና መከበር የሚያደረገውን ትግል በሙሉ ልባቸው እንዲደግፉት ግዴታ የሚጭንባቸው። ይህን ሃቅ በተለይ ለአማራው ከዛም ለኢትዮጵያ እናስባለን የሚሉ ሌሎች ዜጎች በሙሉ ሊያጤኑት ይገባል። Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Related Posts የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 16, 2025 የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 16, 2025 የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! March 11, 2025 Previous Story ትረካ – አገሪቷን በዝርፊያ ያጠቧት አባት እና ልጅ | አርአያ ተስፋማርያም Next Story ከዋቃ ጉራቻ ወደ ዋቃ ዳለቻ:- የድህነት ወይስ የትንቢት እዳ? Latest from Same Tags የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡ 10 የአማራ ህዝብ የህልወና አደጋ ምንጮች ብዙ ናቸው። ሁሉን አደጋዎች በአንድ ጊዜ መጋፈጥ አይቻልም። • በአሁኑ ወቅት የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017በአንዳርጋቸው ጽጌክፍል ፡ 9 ወዳጅ ማብዛት ጠላትን መቀነስ፤ የአማራ ስትራተጂ እንኳን ለህልወናው መከበር የሞት የሽረት ትግል የሚያደርግ የአማራ ህዝብ ቀርቶ፣ በሁሉም ዘርፎች የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል 4 ፡የአማራ ትግልና የፋኖ ማኒፌስቶ በተደጋጋሚ አማራ የትግል ማኒፌስቶ የለውም የሚለው ጉዳይ ይነሳል። አዎ የለውም። ይህ ማለት ሁሉም የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡2 ያለፈው እና መጪው ዘመን ለአማራ፤ ነብይ፣ ጠንቋይ፣ ሳንቲስት መሆንን አይጠይቅም። ያለፉትን መቶ ለመሙላት ጥቂት አመታት የቀረውን ዘመን የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ከአጻጻፍና ከይዘት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሀ) የቅርጽ ጉዳይ የማንበብ ባህል እየተዳከመ መጥቷል። በመሆኑም ሰፊ ትንታኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በአጭሩ ጨምቆ
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡ 10 የአማራ ህዝብ የህልወና አደጋ ምንጮች ብዙ ናቸው። ሁሉን አደጋዎች በአንድ ጊዜ መጋፈጥ አይቻልም። • በአሁኑ ወቅት
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017በአንዳርጋቸው ጽጌክፍል ፡ 9 ወዳጅ ማብዛት ጠላትን መቀነስ፤ የአማራ ስትራተጂ እንኳን ለህልወናው መከበር የሞት የሽረት ትግል የሚያደርግ የአማራ ህዝብ ቀርቶ፣ በሁሉም ዘርፎች
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል 4 ፡የአማራ ትግልና የፋኖ ማኒፌስቶ በተደጋጋሚ አማራ የትግል ማኒፌስቶ የለውም የሚለው ጉዳይ ይነሳል። አዎ የለውም። ይህ ማለት ሁሉም
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ክፍል ፡2 ያለፈው እና መጪው ዘመን ለአማራ፤ ነብይ፣ ጠንቋይ፣ ሳንቲስት መሆንን አይጠይቅም። ያለፉትን መቶ ለመሙላት ጥቂት አመታት የቀረውን ዘመን
የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች! ቀን የካቲት 2017 በአንዳርጋቸው ጽጌ ከአጻጻፍና ከይዘት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሀ) የቅርጽ ጉዳይ የማንበብ ባህል እየተዳከመ መጥቷል። በመሆኑም ሰፊ ትንታኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በአጭሩ ጨምቆ