የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ፓዎር ቻይና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ግንባታ ለማከናወን የ125.6 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ኮንትራት ተፈራረሙ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
የኮንትራት ሥምምነቱ የተደረገው የውሃ መቀበያ አሸንዳዎችን እና የመቆጣጠሪያ በሮችን እንዲሁም የአስራ አንድ የኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን የዲዛይን፣ የአቅርቦት፣ የገጠማ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ሥራዎችን ለማከናወን እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከሁለት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ጂ.ኢ ሃይድሮ ፍራንስ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አምስት ኃይል ማመንጫ ዩኒቶች ተርባይን ጀነሬተሮችን ለማምረት፤ ለመግጠምና ለመፈተሸ የሚያስችል የ53 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት መፈራረማቸውን ዘ-ሐበሻ ዘገቦ ነበር::
–