የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው በሰላም ተመለሱ::
የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን በትናንትናው ዕለት ከጎንደር የጀመሩት መሪዎቹ በባህር ዳር ከጠሚር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በመሆን በሶስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ ውለው ሀገራቱ የደረሱትን የሶስትዮሽ ስምምነት አፈፃፀም ላይ ተነጋግረዋል:: መሪዎቹ ከውይይታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ የኢኮኖሚ ትብብርና ቀጠናዊ ሰላምን የማስጠበቅ እቅድ በሚገባ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “ከሁለት ወር በፊት በጋራ በነደፉት እቅድ አተገባበር ላይ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: እቅዱ በተቀመጠው ልክ እየተተገበረ ይገኛል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል::” ካሉ በኋላ ከሶማሌያ ፕሬዚዳንት ፈርማጆ ጋር በመሆኑ በኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረውን ማእቀብ ሊያነሳ መሆኑን “የማእቀቡ መነሳት የአከባቢውን ሰላም፣ ልማትና ትብብር እንደሚያሳድገውም በመግለጽ” በአድናቆት እንደሚያዩት ገልጸዋል::
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ያሰራውን አዲስ ሆስፒታል ከሁለቱ መሪዎች ጋር መርቀው ከከፈቱ በኅውላ ለጥበበ ግዮን እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምሩቃኑ በተማሩበት ሙያ ስራ ከመጀመራቸው በፊት የሶስቱን አገራት ጥምረት ለማጠናከር ወደ ሶማሊያና ኤርትራ በመሄድ በሙያቸው ለጥቂት ጊዜ እንዲያገለግሉ ጥሪ ጥሪ አቅርበው በተማሪዎቹ ዘንድ አዎንታን አግኝተዋል:: በዚህም መሰረት ሃምሳ ሃምሳ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ወደ ኤርትራና ሶማሊያ ተጉዘው ለተወሰነ ጊዜ የነፃ ህክምና በመስጠት እንደሚያገለግሎ ተገልጿል::
https://www.youtube.com/watch?v=ZvwwoqvPgSg