በሌብነት እና በሌሎች ወንጀሎች የሚፈለጉ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አመራሮች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው:: መቀሌ ላይ የተደበቁትን ለመያዝ አንድ ልዩ ኃይል ወደዚያው ማቅናቱ ተሰማ::
ከአርባ በላይ የሚሆኑ የጀነራልነት የኮለኔልነትና ሌሎችም ማዕረግ ያላቸው ከአርባ በላይ የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በትናንትናው ዕለት ለስብስባ ተጠርተው በዚያው ታፍሰው እንደታሰሩ መረጃዎች ወጥተዋል:
በመከላከያው አመራር ውስጥ የነበረውን የአንድ ብሄር የበላይነት አስወግጃለሁ በሰራዊቱ ውስጥ ያመጣነውን ለውጥም በኩራት እናገረዋለሁ ያሉት ዶ/ር አብይ አህመድ በሌቦች ላይ የሚወሰድ እርምጃ በቅርብ እንደሚኖር ሲናገሩ ቆይተዋል:: እስካሁን እነዚህ የጦሩ ከፍተኛ መኮንኖች ለምን እንደታሰሩ ይፋዊ የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም ፖሊስ የፊታችን ሰኞ ለጋዜጠኞች ስለተጠረጠሩበት ወንጀል መግለጫ ይሰጣል::
የፌዴራሉ መንግስት የፌዴራል እስር ቤት የሆነውን ማዕከላዊን በመዝጋቱ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ፖሊስ ታስረው የሚገኙት የጦር መኮንኖች መካከል የአስራ አራቱ ስም ዝርዝር ደርሶናል::
1. ብ/ጀ/ ጽጋቡ ፈትለ የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ
2. ኮ/ል ሙዕዝ የሎጂስቲክስ ክፍል ኃላፊ
3. ኮ/ል በረሃ የሜጋ ፕሮጅክቶች ኃላፊ
3. ኮ/ል ሙሉ የሰው ሃይል አስተዳደር ኃላፊ
4. ኮ/ል ተክላይ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍል ኃላፊ
5. ኮ/ል በረሃ የሕግ ክፍል ኃላፊ
6. ኮ/ል መሃመድ የስነምግባር ክፍል ኃላፊ
7. ኮ/ል ህሉፍ የኮንትራት አስተዳዳር ኃላፊ
8. ሌ/ኮ አክብረት የእቅድ ዝግጅት ኃላፊ
9. ሌ/ኮ ተከስተ የአቅም ግንባታ ማእከል ኃላፊ
10.ሺ አለቃ ገብረስላሴ የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ
11. ሺ አለቃ ክፍሌ የቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ
12. ሺ አለቃ መኮንን
13. ጀኔራል ሀድጉ ገ/ስላሴ
14. ጀነራል ጠና ቁርንዲን ሲሆኑ ተጨማሪ በወንጀል የተጠረጠሩ እና መቀሌ ላይ ተደብቀው የሚገኙትንም ለመያዝ አንድ ልዩ ግብረኃይል ወደ ዚያው ማቅናቱም ተሰምቷል:: ከዚህ ቀደም መቀሌ ላይ ወንጀለኞችን ለመያዝ የሄዱ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በትግራይ ክልል ፖሊሶች መታሰራቸውን ዘ-ሐበሻ ዘግቦ የነበረ ሲሆን አሁን ወደዚያው የሄደው ግብረኃይል ተመሳሳይ ችግር ያጋጥመው አያጋጥመው የታወቀ ነገር የለም::
መቀሌ ላይ በርካታ በሌብነት የሚጠረጠሩ የጦሩ መኮንኖች ተደብቀው እንደሚገኙ ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ሲያጋልጥ መቆየቱ ይታውሳል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ዛሬ ከታሰሩት መካከል የቀድሞው የደህንነት ዳይሬክተር ጌታቸው አስፋ ምክትል እና ቀኝ እጅ የነበረው ዶ/ር ሀሺም እንደሚገኝበት ታውቋል::ዶ/ር ሀሺም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ ዋና እና ቁልፍ ሰው እንደነበር ይነገራል:: ጌታቸው አሰፋ የሚያምነውና የሚተማመንበት ዋነኛው ሰው ነው የሚባለው ዶ/ር ሃሺም በሰው ኃይል ምልመላ፣ መረጣ፣ ስምሪት፣ ስልጠና፣ የመስሪያ ቤቱ አጠቃላይ አደረጃጀት፣ መዋቅርና የውጭ ግንኙነት በበላይነት የሚመራ ነበር ተብሏል::
https://www.youtube.com/watch?v=ZvwwoqvPgSg