መምህር ግርማ ወንድሙ በነጻ ተለቀቁ

November 10, 2018

ዛሬ ለንባብ የበቃው ኢትዮጲስ ጋዜጣ መምህር ግርማ በነፃ መለቀቃቸውን ዘገበ። እንደጋዜጣው መምህር ግርማ ወንድሙ ነፃ የወጡት ከተከሠሡበት የወንጀል ክስ ነው። ለሶስት አመታት ከገንዘብ ማጭበርበር ጋር የተያያዘውን ጨምሮ ስምንት የተለያዩ ክሶች ቀርበውባቸው ፍርድ ቤት ሲመላለሡ ነበር ያለው ጋዜጣው ጥቅምት 28 ቀን 2011 ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ነፃ እንደተባሉ ገልፆዋል። በክሡ ምክንያት ከአገር እንዳይወጡ ተጥሎባቸው የነበረው የጉዞ እግድም ተነስቶላቸዋል ብሏል።

መምህር ግርማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሥቲያን ዘንድ በአገልግሎታቸው የሀይማኖቱን ሥርአት የተከተሉ አይደሉም በሚል በተደጋጋሚ ነቀፌታ የሚቀርብባቸው መሆኑን ያወሣው ጋዜጣው ያስተምሩባቸውና ያጠምቁባቸው ከነበሩ እስጢፋኖስና የረር ሥላሤ ቤተክርሥቲያናት መታገዳቸውንም ጠቅሷል። እሥጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በታገዱበት ወቅት በርካታ ተከታዮቻቸው “የፈውስ አገልግሎቶቹ ያናደዳቸውና በመምህሩ ተደማጭነት ቅር የተሠኙ የቤተክርስቲያኗ አመራሮች ናቸው በተንኮል ያስነሷቸው” በሚል ተቃውሞ ማሠማታቸውን ኢትዮጲስ አውስቷል።

https://www.youtube.com/watch?v=ZvwwoqvPgSg

Previous Story

ኢትዮጵያ ስለምታቋቁመው የባህር ሃይል ማብራሪያ ተሰጠ | ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ቤተመንግስት የሄዱት ወታደሮች ጉዳይም ተናገሩ

Next Story

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው በሰላም ተመለሱ

Go toTop