Sport: ኢትዮጵያ ዛሬ በሜዳሊያዎች ተንበሸበሸች

August 17, 2013

(ዘ-ሐበሻ) በሞስኮ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት መሠረት ደፋር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ስታስገኝ በወንዶች ማራቶን ደግሞ ኢትዮጵያውያኑ ሌሊሳ ዴሲሳ እና ታደሰ ቶላ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመውጣትየብር እና የነሃስ ሜዳልያዎችን አስገኝተዋል።

በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ እንደተለመደው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መሰረት ደፋር ኬንያዊቷን አስከትላ አንደኛ በመሆን ስታጠናቅቅ መሰረት ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ እና 20 ማይክሮ ሰከንድ ለመፈጸም ችላለች። መሰረትን ተከትላ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አልማዝ አያና ሶስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳሊያዎችን አምጥተዋል።

በሞስኮ እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ 3 ወርቅ ፣ 3 ብር እና 3 የነሃስ ሜዳልያዎችን አግኝታለች።

Previous Story

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ

Next Story

በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን በጎርፍ አደጋ 28 ሰዎች ሞቱ

Go toTop