የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ፮ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ

July 1, 2015

እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባሎች፣ ሰኞ ሰኔ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓም (June 29, 2015) በድርጅቱ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 20.2(1) መሠረት የምክር ቤቱን ፮ኛ መደበኛ ስብሰባ በአካል በድርጅቱ ጽሕፈት ቤት በመገኘት እና በዘመኑም ቴክኖሎጂ በመጠቀም አካሂደናል።
በስብሰባችን በተያዙት አጀንዳዎች መሠረት ተወያይተን የሚከተሉት የአቋም ውሣኔዎች ላይ ደርሰናል።
1. በመካከለኛው ምሥራቅ የአልቃ-ዒዳ ተቀጥላ በሆነው ዳኤሽ (አይ.ሲ.ሲ.) አማካኝነት በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በተለያዩ ነባር ኃይማኖቶች ተከታይ ሕዝብ ላይ ያስከተለው ፍጅት እና ስደት፣ በነባር እና ጥንታዊ ታሪካዊ ቅርሦች ላይ ያደረሰው ውድመት አሳዝኖናል። በዚህ ዓመት በሚያዝያ ፲፮ ቀን ባወጣነው ፲፬ኛ መግለጫችን ድምፃችንን ከፍ አድርገን እንዳሰማነው፣ ከሁሉም በላይ በጦርነቱ የመጀመሪያ መሥመር ተጠቂ የሆኑት አገር አልባዎቹ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሲሆኑ፣ በተለይ ደግሞ በሊቢያ በዳኤሽ አማካይነት በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሠቃቂ የግፍ ግድያ ሐዘናችንን እጅግ የከበደ አድርጎታል። የደቡብ አፍሪቃ ዜጎች ለነፃነታቸው በሚታገሉበት ዘመን እኛ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድጋፍ ካደረግንላቸው አገሮች መካከል ቀዳሚዎች ነን። ሆኖም ዛሬ እነርሱ ነፃ አገር ሲሆኑ፣ በደቡብ አፍሪቃ ተጠልለው በሚኖሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመው የግፍ አገዳደል፣ ኢትዮጵያዊነት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገሮች ገሃነም የወረደበት ሆኖ ተሰምቶናል። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በዓለም ዙሪያ፣ በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ፣ የሚፈሰው የንፁሐን ደም እንዲቆም ጥሪውን ያቀርባል። ስለሆነም በዓላማችን በግልፅ እንደሠፈረው፣ የሰዎች የዕምነት ነፃነት እንዲከበር፣ በሕዝቦች መካከል ወንድማማችነት፣ ፍቅር እና መተሳሰብ እንዲሰፍን ከሚጥሩ ኃይሎች ጎን በመቆም የበኩላችንን ድርሻ ለማበርከት እንንቀሣቀሳለን። ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያውያን ስደት፣ መከራ እና ሥቃይ እንዲያበቃ፣ የስደቱና የመከራው ምንጭ የሆነው የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ አሽንቀጥሮ ለመጣል በዘር ጠላትነት ተፈርጆ የዘር ጥፋት የተፈጸመበትን የዐማራ ነገድ በማደራጀት የትግሉ ግንባር ቀደም ተዋንያን እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል እንገባለን።

2. የትግሬ ወያኔ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጠላት በመሆኑ፣ ይህ ዘረኛ ቡድን በሕዝባችን ላይ በመፈጸም ላይ ያለውን የአገር ክህደት፣ የንብረት ዘረፋ፣ በሙስና መዘፈቅ፣ በሕዝብ ላይ የጅምላ ግድያ እና እስራት መፈጸም እየተከታተልን ለዓለም ኅብረተሰብ እና ለተበዳዩ ሕዝባችን የማጋለጥ ሥራችን አጠናክረን እንቀጥላለን።

3. ዐማራው በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን በዘር ጠላትነት ተፈርጆ፣ የተፈጸመበትን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ትውልዱ ጠንቅቆ እንዲያውቅ እና የወያኔን ትውልድ በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ተጠያቂ ማድረግ የሚችልበትን መረጃዎች የመሰብሰብ እና የመተንተን ሥራችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናደርጋለን።

4. በጎጃም፣ በጎንደር፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በሐረርጌ እና በሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች በትግሬ-ወያኔ እና በተባባሪዎቹ አማካይነት በወገኖቻችን በዐማራ ነገድ ተወላጆች ላይ የቀጠለውን የጅምላ ግድያ እና ማፈናቀል አጥብቀን እናወግዛለን።

5. የትግሬ-ወያኔ ሎሌ የሆነው የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን በግድምድሞሽ እንዳመነው፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ለሱዳን እስላማዊ አገዛዝ አሣልፎ የመስጠቱን ተግባር፣ ይዋል ይደር እንጂ የትግሬ-ወያኔ እና ተላላኪዎቹን በአገር ክህደት ወንጀል የሚያስጠይቃቸው እንደሆነ እናስገነዝባለን።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

Previous Story

የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው

Next Story

በጭልጋ የቅማንት ማህበረሰብ አባላት አሁንም በሕወሓት መንግስት ታጣቂዎች እየተገደሉ ነው

Go toTop