በጭልጋ የቅማንት ማህበረሰብ አባላት አሁንም በሕወሓት መንግስት ታጣቂዎች እየተገደሉ ነው

July 1, 2015

የትህዴን የመረጃ መረብ እንደዘገበው በሰሜን ጎንደር ዞን፤ ጭልጋ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የቅማንት ብሄረሰብ አሁንም ራሳችን ነው የምንተዳደረው በማለታቸው ብቻ በስርዓቱ ታጣቂዎች እየተገደሉ መሆናቸው ተገለፀ።
በአማራ ክልል፤ ጭልጋ ወረዳ የሚገኙ የቅማንት ብሄረሰብ ህገመንግስት በፈቀደው መሰረት ራሳችንን እናስተዳድራለን ብለው ለጠየቁት አወንታዊ መልስ ስላላገኙበት ተቃውሞ ለማካሄድ በተንቀሳቀሱበት ግዜ በስርዓቱ ካድሬዎችና ታጣቂዎች በተቶኮሰ ጥይት በርካታ ንፁኃን ዜጎቻችን መገደላቸው ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ የመግደል እርምጃ ከግንቦት ወር 2007 ዓ/ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆንን የገለጸው መረጃው ባገራችን ውስጥ በቋንቋችን የመማርና ራሳችን የማስተዳደር መብታችን ይከበርልን በማለት በተለያዩ ብሄረሰቦች የሚነሳውን ህጋዊ ጥያቂ አስካሁን መልስ እንዳላገኘና አሁንም ጥያቄው እየቀጠለ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።

Previous Story

የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ፮ኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ

Next Story

And oh, what heights we’ll hit

Go toTop