ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው አስራት አብርሃም ዳኛዋ እንዲለቀቅ ቢወስኑም ፖሊስ በእምቢተኛነት አሳድሮ በዛሬው ዕለት ለቆታል፡፡
አስራት አብርሃም
የመድረክን ሰላማዊ ሰልፍ በመቀስቀስ ላይ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በመታሰራቸው ከአንድ የአረና ፓርቲ አመራር ጋር ለጥየቃ ያመራው ፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃም በጣቢያው መታሰሩን ቤተሰቦቹና የአንድነት አመራሮች ሊጠይቁት እንደሄዱ የከተማይቱ ፖሊስ ‹‹አስራት አብርሃም›› የሚባል ሰው አለማሰሩን በመግለጽ አስራትን መሰወሩን መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
እንዲህ የሚባል እስረኛ አላሰርኩም ያለው ፖሊስ አስራትን በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡ በፍርድ ቤት የቀረበው የአንድነት ፓርቲ አባል ምሽቱን በፖሊሶች መደብደቡንና ፖሊሶቹም ለሊት ህክምና እንዲያገኝ ወደ ክሊኒክ እንደወሰዱት አጋልጧል፡፡
አንድ ፖሊስ ‹‹ሰድቦኛል››በማለት ክስ የመሰረተበት አስራትን በ500 ብር ዋስ እንዲፈታ ክብርት ዳኛዋ ቢወስኑም ፖሊስ በእምቢተኛነት አሳድሮ በዛሬው ዕለት ለቆታል፡፡