በትግራይ ክልል ውስጥ አንድ የመንግስት ሚሊሻ ወታደር አንዱን ባለስልጣን መገደሉን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ዘገበ።
የአረና ለትግራይ አመራር አባል የሆነው አብርሃ በላይ እንደገለጸው በመንግስት ሚሊሻ የተገደለው የትግራይ ክልል ውሃ ሃብት ኢንተርፕራይዝ ባለስልጣን አቶ አያሌው ደስታ ነው። እንደ ዘገባው ከሆነ የትግራይ ክልል የውሃ ሃብት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጸምባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል ግንባር ቀደሙ ሲሆን “ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም” እንደሚባለው ባልሰልጣናቱ እርስ በእርሳቸው በተደጋጋሚ ይጣላሉ።
በሚሊሻ ወታደሩ የተገደለው አቶ አያሌው ደስታ የሳርት ፕሮጀክት መሃንዲስ እንደነበር የሚገልጸው ዘጋቢው አብርሃ የመስሪያ ቤቱ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እርስ በእርስ ከመጋጨታቸው ውጪ አቶ አያሌው በምን ምክንያት የተነሳ በሚኒሻው ሊገደል እንደቻለ የታወቀ ነገር የለም።
አቶ አያሌው የተገደለው ትናንት ለሊት ነው።
ዘ-ሐበሻ በግድያው ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ካገኘች ይዛ ትመለሳለች።