ከዲ/ኤፍሬም ስለሺ
መጀመሪያ ከታናናሾቹ ጀመሩ፡ “ልጅ ያቦካው፡ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጀርባ ወያኔ አለ እያሉ የቤተክርስቲያንን አንድነትን የጠየቁትን ወጣቶችን ሁሉ ተሳደቡ፡ ሲፈልጉ “ልጅ ያቦካው” ሲፈልጉ ከፋፋይ፡ አክራሪ ያደርጓቸዋል፡ ሲፈልጉ ደግሞ ያልተማሩ ሰሜታውያን ያደርጓቸዋል። ዝም ሲሏቸው እንደ ተሰጣቸው ኃላፊነት የቤተክርስቲያንን አንድነት ሊያስተምሩ በተነሱ ካህናት ላይ ድግሞ ዘመቱ፡ ግማሹን ሲያሳግዱ ግማሹን በስልክ የሞት ዛቻ ሲሰጡ ግማሹን “የ ፖሎቲካ ትምህርት” ነው ሲሉ፡ ግማሹን መስቀሉ የግል ይመስል “የእርሶን መስቀል አልሳለምም” ሲሉ ሰነበቱ። በአደባባይ በጀብድ “ካህናቱ ጠግበዋል እነሱን አባረን የተራቡ ካህናት እናመጣልን” እያሉ ፎከሩ። በየ ሚዲያው የቤተክርስቲአንን ካህናትና አንድነትን የናፈቀውን ምዕመን ተሳደቡ። የቤተክርስቲያንን ልዕልናና ክብር ሳይጠብቁ ውሸቱን ከሃይማኖት እየቀላቀሉ፡ ወይም ደግሞ ግማሽ እውነት ይዘው ከፖለቲካው እሳት ጋር እያጋጩ መንጋውን አስጨነቁ። ይባስ ብለው እራሳቸውን “የአባቶች አስታሪቂዎች እኛ ገልለተኞች ነን” ካሉ በኋላ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አራሱን ቤዛ አድርጎ በሰጠበት ዕለተ መድኃኔዓለም፡ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሊያስተምሩ ሊባርኩ ቢመጡ እግዚአብሔርን ሳይፈሩ ሰውንም ሳያፍሩ በቅድስናው ስፍራ በጫማቸው በመግባት የቀበሌ ሜጋ ፎን ይዘው ጮሁ ተሳደቡ፡ የሌባ ጣታቸውን ቀስረው ሊቀ ጳጳሱን “ሌባ ሌባ” አሉት። ጌታ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሏልና፡ ብጹዓን አባቶች ዲያቆኑ አድንኑ ካለ በኋላ የሰደቧቸውን ወደ ታች እየተመለከቱ በትህትና “አቤቱ ሕዝበህን አድን ርስትህንም ባርክ ጠብቃቸው እስከዘላለምም ድረስ ከፍ ከፍ አድርጋቸው” ብለው መረቁው ጸሎት አሳረጉ። ስራቸውንም እንደ ጀብድ “ኃይ ፋይቭ” እየተሰጣጡ ወጡ፡ እንደ መልካም ዜናም ቪዲዮውን አሰራጩት። ቅዱስ ሲኖዶስ አስተምሩ ብሎ በላካቸው መሠረት፡ ከ ቤተክርስቲያን ቀኖናና ከ ሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ምክርና ተግሣጽ ርቆ የመኖር “የገለልተኝነት” አቋም ቀርቶ ጌታ በደሙ በዋጃት፡ ሐዋርያት ደግሞ በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንጠቃለል ዘንድ አስተምረው እንደሄዱ፤ በጠበቃቸው በኵል ሊቃነ ጳጳሳት ቤተክርስቲያን እንዳይመጡ አሳገዱ። በቅዳሴ መካከል ጣልቃ በመግባት ድሮ ድሮ በሂደት ይስተካከላል “ሰም መጥራት ብቻ ነው የቀረው” በሚል ሽፋን ይስተካከላል ተብሎ በትዕግሥት የቆየውን ሥርዓት ፤ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ከፍርድ ቤት በተጻፈ እገዳ ካህናቱ በቅዳሴው ሥርዓት ላይ የቅዱስ ፓትርያርኩ ስም እንዳይጠራ አሳገዱ።
በዚህ ጊዜ እለቱ አርብ ነውና ጭንቀት መጣ፡ ካህናቱ የሊቀ ጳጳሱን ትዕዛዝና ሕገ ቤተክርስቲያን ይከተሉ ወይስ ከፍርድ ቤት የመጣውን እገዳ? ይህ ጊዜ አጣብቂኝ ነበር። የጠበበችው በርና ሰፊዋ በር እንደ አማራጭ መጡ፡ ይህ ጊዜ ዮሐንስ ከ ይሁዳ ተለየ፡ ይህ ጊዜ አቋም ተለየ ፡ማን ከማን ጋር እንደሚቆም ተለየ። ቤተክርስቲያንን እንደ ቤተክርስቲያንነቷ ያከበሯት ካህናት ንብረቴ ትዳሬ ገንዘቤ ሳይሉ በጠበበችው በር ገቡ። የሰው ፊት እየገረፋቸው እውነተን መሰከሩ፡ ያስተማሩትን በተግባር አሳዩ። ከ ፲፬ቱ ማኅበረ ካህናት የተለዩት ፬ቱ ካህናት ግን ሥልጣን፡ ገንዘብ፡ ዝናን ያተረፉ መስሏቸው የቤተክርስቲያንም አንድነት በግልጽ ተቃወሙ። ይሁዳ ኑሮው አገልግሎቱና አዳሩ ከሐዋርያት ጋር ነበር፡ አርብ ቀን ስትመጣ ግን ከ ቀያፋና ሐና ጋር ቆመ፡ እነዚህም ፬ ካህናት ውሏቸው አገልግሎታቸው ልሳናቸው ከ፲፬ቱ ማኅበረ ካህናት ጋር ነበር፡ ዛሬ ግን ዕለቱ አርብ ነውና “ጳጳስ የለም” “ጳጳሱ ሌባ ነው” ጳጳሱን “አንተ” ብለው ከተሳደቡት ጋር አብረው ሆነው የገዛ ወንድሞቻቸውን ካህናት “ስቅሎ ስቅሎ” አሉ። እነዚሁ አካላት ትናንተና ገንዘባቸው እንዲቆረጥ፡ ክበራቸው እንዲገፈፍ፡ በክህነታቸው እንዳይከበሩ አንዴ “መረጃ አለን” አንዴ “አባሯቸው” አንዴ “እሱ ሌባ ነው” የሚሏቸው አካላት ነበሩ። ዛሬ ግን ቤተክርስቲያንን ይከሱ ዘንድ አብረው ተማከሩ። ጌታ ግን ከባቴ አበሳ፡ ኃዳጌ በቀል (ኃጢያት የሚሸፍን በቀል የሌለበት) እንደሆነው ሁሉ አብረዋቸው ሌሊት እና ቀን የሚያገለግሉት( በተለይ ቋሚ ካህናቱ) ለአመታት ሁሉን ሸፈኑት ሁሉን አለፉት ሁሉንም ቻሉት።
ከ ፲፬ቱ ማኅበረ ካህናት ጋር በቤተክርስቲያን አንድነት አልተባበርም ያሉቱ ፬ቱ ካህናት ከሊቀ ጳጳሱ ትዕዛዝ ውጪ ሲውጡ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ።
ያ አልበቃ ብሎ “በቅደሴ ሥርዓት ውስጥ ያለው ቅዱስ ፓትርያርክን ስም እንደ መጽሐፉ መጸለይ “ትውፊት” ነው፡ ሊቃነ ጳጳሳት ባንዳዎች፡ ሃሰተኞች፡ ወያኔዎች ናቸው እያለ ሲናቀፍ ሲሳደብ ቆይቶ የፕሮቴስታንትና የኢሳትን መግለጫ እንደ ቤተክርስቲያን የመጨረሻ መረጃ ሲያቀርብ ኖሮ በአለፈው እሁድ በድምፅ ሬድዮ ወጥቶ ግዝቱ “ወፈ ግዝት ነው፡ እንዳውም ዛሬ ሊቀ ጳጳስ የሚባል የለም” ብሎ ካደ። ያ አልበቃ ብሎ ትናንት ሊባርኩን በመጡ ቁጥር “ወያኔ ናቸው፡ አንፈልጋቸውም፡ ምንም አይነት ድርጎ ልንሰጣቸው አይገባም” ሲሉ የቆዩ አካላት ዛሬ ደውለው ግማሽ ታሪክ በመንገርና እውነቱን በማጣመም እየተቀዱ እንደሆነና ለአለም ድረ ገጽ እንደሚበትኑት ሳይነጕራቸው “መርጌታውን ሊቀ ጳጳሱ አወገዙ ይባላል ምን ይመስሎታል” በለው ጠየቋቸው። አይደለም ከሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ቀርቶ ከመላው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እርሳቸውን ለማጣላት የራቸሳቸውን የግል አስተያየት ተጠቅመው አንድነትን የናፈቀውን የሕዝበ ክርስቲያኑን ሕልም ያጨለሙ መስሏቸው አዲስ ሰይፍ ይዘው ተነሱ። በነገራችን ላይ መሪጌታው አው አልተወገዙም! ሥልጣነ ክህነታቸው ግን ተይዟል” መወገዝ ሌላ ነገር ሥልጣነ ክህነት መያዝ ደግሞ ሌላ ነገር። አማረኛው ሁለቱን ነገሮች ለይቶ ስም ሰጥቷል፡ አንዱን ውግዘት” አንዱን ደግሞ “ሥልጣነ ክህነት መያዝ” ይባላል። አንድ ካህን ሥልጣነ ክህነቱ ተያዘ ማለት የክህነት ሥራን መስራት አይችልም እንጂ ተወግዟል አይባልም። With that said the English word “excommunication goes for both meaning. the word Excommunication can be used for both the word ውግዘት and ሥልጣነ ክህነት መያዝ In case of the Merigeta and three other priest’s excommunication that came from the Archbishop፣ is restriction from practicing the acts of priesthood. (ሥልጣነ ክህነት መያዝ) ። ስለዚሀ መርጌታው ሊቀ ጳጳሱን በመተላለፋቸው ሥልጣነ ክህነታቸው ቤተ መቅደስ ከመግባት፡ ታቦት ከመዳሰስ፡ ቀድሶ ከማቊረብ፡ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ እንጂ አልተወገዙም። ውጉዝ ከመአርዮስ አልተባሉም። ሥልጣነ ክህነታቸው ነው የተያዘው። ምዕመን የመሆን በቤተክርስቲያን መመላለስን አልተከለከሉም ያም ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ አሁንም ቢመለሱ እውነተኛይቷን ወንጌለ መንግሥት አብረው ከሌሎቹ ወንድሞቻቸው ጋር ቢያስተምሩ እናት ቤተክርስቲያን ሥልጣነ ክህነታቸውን እንደምትመልስ እጆችችዋን ዝርግታ እንደምትጠብቅ የሊቀ ጳጳሱ ደብዳቤ ይናገራል። (ስለ ግዝትና ሥልጣነ ክህነት መያዝ ለይተው ሊቃውነቱ እራሳቸው ስለሚያስተምሩን እኔ ወደዛ አልገም።) ግን አሁንም ቢሆነ ቅንጭብ እውቀት ይዞ በሬድዮ መቅረብ እራስን ያስገምታል።
መሪጌታ
መሪጌታ የተያዘው ሥልጣነ ክህነትዎ እንዲመለስ ባለፈው ብጹዕ አቡነ ዘካሪያስ ጋር ልክ እንደደወሉት፡ ለቅዱስ ሲኖዶስም አቤቱታ ማቅረብ ሲገባዎት የኢየሩሳሌም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታችን ብጹዕ አቡነ ዳንኤል ጋር ደውለው ስለ “ውግዘትዎት” ሲያስጠይቁ
፩- አንድ የሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያወገዘውን ካህን ወይም ሥልጣነ ክህነቱ የተያዘበትን ካህን ሌላ ማንም ሊቀ ጳጳስ እንደማያፈተው በቀሲስ ዶክተር መስፍን ጉዳይ ላይ ይናገሩና ያስተምሩ አልነበርም? (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፬ ቁ፷፩)
፪- አንደ የቅዱስ ሲኖዶስን አባል በማታለል፡ እውነቱን በማጣመም እናንተ ባቀረባችሁላቸው ክፉ ወሬ ተነስተው የራሳቸውን የግል አስተያየት ቢሰጡ ቀድታችሁ ለአለም ስታሰራጩ አይደለም ከሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዛካሪያስ ጋር ከመላው ቅዱስ ሲኖዶሰ ጋር እንደምታጣሏቸው ይህን አያውቁም? ነው ወይስ የዚህ አልበቃ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስንም እንክፈለው?
እሺ እኛ “ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም” ወይም አክራሪዎች ስሜተኞች እንሁን። ለቤተክርስቲያን አንድነት ንብረቴ ገንዘቤ ሳይሉ የቆሙላት ካህናት ድግሞ “ወያኔ” አላችሁ፡ በየሚዲያውና አለማዊ ደረ ገጽ የቤተክርስቲያንን ልጆች አዋርዳችሁ፡ ሊቃነ ጳጳሳቱንም በቅድስናው ስፍራ ሰደባችሁ አሁን ታዲያ ሕግጋቷንና ቅዱሳት መጻሕፍቷን ለራሳችሁ እንዲመች ስታጣምሙት ዝም እንበላችሁ? (፩ ጴጥ ፪፡፲፩)
መሪጌታ ብዙ ሰው አለቀሰቦት ብዙ ሰው ቆሰሎቦት ብዙ ሰው ጠፋቦት፡
ግን እኮ አለ ቅዱስ ፖሊካርፐስ፡ ግረፉን፡ በመጋዝ ሰንጥቁን ለአናብሰት አሳልፋችሁ ስጡን በእሳት አቃጥሉን በሰይፍ ሰይፉን..ነገር ግን…እናንተ በገረፋችሁን በመጋዝ በሰነጠቃችሁን ለአናብስት አሳልፋችሁ በሰጣችሁን በእሳት ባቃጠላችሁን በሰይፍ በሰየፋችሁን ቁጥር እኛ እየበዛን እንሄዳለን፡ ለምን ብትሉ የቅዱሳን ደም ለቤተክርስቲያን ጌጧና ውበቷ ነው፤ የክርስቶስ ክብር መገለጫዋ ነው። (ቅዱስ ፖሊካርፐስ)
የሚደንቀው ነገር ግን ክብር ለመድኃኔዓለም በትግል ብዛት አትወሰንም ቅድስት ቤተክርስቲያን፡ አንድነት ይመጣል፡ እውነቱም ይገለጣል!
የቅዱሳን አምላክ ማስተዋሉን ትንሽ፡ እንዳው ትንሽ ብቻ!! ለሁላችንም ይስጠን።