ከጭልጋ ከተማ ርቃ የምትገኝ የገጠር ከተማ የሆነችው ጮንጮቅ በ15/08/2006 አ.ም በገበሬዎችና በፌድራል ፖሊሶች በተፈጠረ የትኩስ ልውውጥ የብዙ ሰዎች ህይወት ሲቀጠፍ ብዙዎችም በከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። የገበሬዎች ቁስለኛም ሆነ የሞተ ወደ ሆስፒታል የሚያደርሳቸው የለም። ከምሽቱ 4:33 እና 5:45 እንዲሁም 7:25 ሰአት … በእነዚህ ሰአቶች ባጠቃላይ 11 መኪኖች ቁስለኛ እና አስከሬን የ2 የጭነት አውሱ አስከሬን የጫኑ ሲሆን 5ቱ አንቡላንስና ከባድና ቀላል ቁስለኞች ይዘዋል። 4ቱ ደሞ አጃቢ የሆኑ የፌድራል ፓሊሶች ናቸው።ይህ በእንዲህ እንዳለ 4 አውሮፕላኖች በተደጋጋሚ በከተማውና በጫካው ሲመላለሱ ያደሩ ሲሆን ማክሰኞ እለት ማታ ከ4:00 ሰአት ጀምሮ ነው። እሁድ እለት ማታ 4 ፌድራል ፓሊሶች ተገለው አስከሬናቸው እንጅ መሳሪያቸው አልተገኘም። በዚሁ እለት 1 ኤሌኮፍተር በጭልጋ ከተማ በሰው ቁመት ሲያንጃብብ አድረዋል።
ሰሜን ጎንደር አከባቢ የምትገኙ ጓዶች ሁኔታውን አጣሩልን።