‹‹የ33ቱ ፓርቲዎች ጥያቄ በአጭር ቃል ሲቀመጥ ‹አሯሯጭነት በቃን!› ነው›› – አቶ ተመስገን ዘውዴ

April 14, 2013

ባለፈው እሁድ በ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፡፡ በመኢአድ፣ በመድረክ፣ በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲዎች ጽ/ቤት በተመሳሳይ ሰዓትና አጀንዳ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባም ‹‹የሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ህግ ያላከበረና ህገ-ወጥ ምርጫ ነው›› በመሆኑም ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዚህ ህገ-ወጥ ምርጫ ባለመሳተፍ ተቃውሞውን ይግለፅ›› የሚል አቋም የተያዘበት ነበር፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባም አቶ ተመስገን ዘውዴ፤ የአንድነት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊና አቶ አሥራት አብርሃ የአረና ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንዲሁም አቶ ስለሺ ፈይሳ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የተመራው ውይይትም ‹‹የኢህአዴግ ህገ-ወጥ ምርጫና በምርጫ ስም የሚፈፀመው ቧልት›› በሚል ርዕስ የአቋም መግለጫ የቀረበበትና ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ውይይት ተደርጐባቸዋል፡፡

‹‹በዚህ ጠባብ ምዕራፍ ውስጥ ሠላማዊ ዴሞክራሲያዊ ትግላችን እንደቀጠለ ነው›› ያሉት አቶ ተመስገን በ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረቡት ጥያቄዎች ‹‹ትክክለኛና የተለሳለሱ ጥያቄዎች ነበሩ›› ሲሉ ነው የገለፁት፡ ፡ ለጥያቄዎቹ ተገቢው መልስ በምርጫ ቦርድ እንዳልተሰጠበት ያስታወሱት አቶ ተመስገን ‹‹ገዢው ፓርቲ ለምናቀርባቸው የተለሳለሰ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ፈንታ በተለመደው ‹‹እኔ አውቅላችኋለሁ›› በሚል ሀገሪቱን ብቸኛ ገዥ በመሆን ለሚቀጥለው 40 እና 50 ዓመታት ለመግዛት ነው የሚፈልገው›› ብለዋል፡፡ ‹‹በአዳራሽ ውስጥ ተሰብስበን ሃሳባችንን እየገለፅን በህግና በሥርዓት እየተወያየን ነው፡፡ ነገር ግን እንደዚህም ሆኖ ፍርሃት እንዲሰማን ሥርዓቱ እያደረገን ነው›› ሲሉ 33ቱ ፓርቲዎች በምርጫው እንዳይሳተፉ ገዥው ፓርቲ እንዳስገደዳቸውና በቀጣይ በሠላማዊና ህጋዊ መንገድ የትግሉን አደረጃጀት ወደ ህዝቡ መድረስ የሚቻልበትን መንገድ አመላካች ሃሳቦች ላይ ውይይት መደረግ እንዳለበት ነው አቶ ተመስገን የተናገሩት፡፡

እናም፤ እንደ አቶ ተመስገን አገላለፅ ደግሞ ‹‹የ33ቱ ፓርቲዎች ጥያቄ በአጭር ቃል ሲቀመጥ ‹አሯሯጭነት በቃን ነው›› ነበር በሌላ በኩል ‹‹ኢህአዴግ በኃይል እየገዛን ያለው የእኛም ትብብር ስላለው ነው›› የሚሉት አቶ አስራት አብርሃ የ33ቱ ፓርቲዎች ቀጣይ ሂደትን በተመለከተ ‹‹ማሰብ ያለባቸው ከአሁን በኋላ ወደ ምርጫ የምንገባው ሜዳውን አስፍቶ፤ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ እንዲሆን ተስማምቶ፣ ለምኖን ሁሉ መሆን አለበት›› ብለዋል፡፡


በተለይ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ጐራ ፖለቲካውን በቆራጥነት ሊመሩ የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጋል ያሉት አቶ አስራት ‹‹ተቃዋሚው በተለይ መተባበር አልቻለም፡፡ ከሀገርና ከዓላማ በላይ የግል ሥልጣን የሚያጓጓቸው ሰዎች አሉ፡፡ የፓርቲ ሊቀመንበር መሆን ከሁሉም ነገር በላይ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን ሰዎች መምከርና
መግራት ያስፈልጋል፡፡ ማስወገድምኢትዮ ቻናል 5ኛ ዓመት ቁጥር 394 ቅዳሜ ሚያዝያ 05/2005 ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም፤ ትግሉ የሚያስፈልገው በቆራጥነት የሚመራውን ነው›› ይላሉ፡፡ ለዚህም ተቃዋሚዎቹ ሁሉ ደካማ ከሆኑ አዲስ ፓርቲ መፍጠር እንደሚቻል ነው የገለፁት፡፡ በተመሳሳይም አቶ ተመስገን ‹‹አመራሩ ለወጣቶች ይለቀቅ በሚለው እስማማለሁ›› ብለዋል፡፡
‹‹እስከዛሬ አንዱ ትልቁ ድክመታችን ወጣቶችን ለማብቃት የተደረገው ጥረት በተቃዋሚ ፓርቲዎች ሂደት ውስጥ ደካማ ነው፡ ፡ ምክንያቱም፤ አንዳንድ ቦታ የእኛም ሂደት ከገዥው ፓርቲ የተለየ ወይም የተሻለ አይደለም፡፡ ይሄን ስልጣን ለወጣቶች የማሸጋገር ሥራ አሁን ከሠራነው በበለጠ በተሻለ መንገድ መሥራት ነበረብን፡፡ ልሠራንም፡፡ ለወደፊት ግን በከፍተኛ ሁኔታ ሊታሰብበት የሚገባ ነገር ነው›› ብለዋል፡፡


አቶ አስራት አብርሃ በበኩላቸው ‹‹ይሄን ህዝብ ማሰለፍ የሚቻለው ሲያምን ነው፡፡ ይሄ አመራር ይሄን ችግር ያወጣኛል የሚል አመራር መፍጠር ያስፈልጋል›› በማለት ‹‹የተሻለ ሰው ሲመጣ እየተቀባበለ የሚሄድበት ትግል መሆን አለበት›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ ‹‹የኢህአዴግ ህገ-ወጥ ምርጫና በምርጫ ስም የሚፈፀመው
ቧልት›› በሚል ርዕስ ባወጣው 10 ነጥብ የያዘ መግለጫም ‹‹የአንድ ሰሞን ግርግር›› ባለው የአካባቢ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ ለይስሙላ የሚከናወን የአንድ ሰሞን ግርግር ሳይሆን ህዝብ ለአስተዳዳሪዎቹ ይሁንታን የሚገልፅበት የዴሞክራሲና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጥያቄ ነው ብሏል፡፡ በምርጫው ሂደትም የህግ የበላይነት አለመታየቱን፣ የምርጫ ቦርድም ገለልተኛ አለመሆኑ፣ ምርጫው አሳታፊ አለመሆኑን በገለፀበት መግለጫው ‹‹ገዥው ፓርቲ ምርጫ ቦርድንና የመንግሥትን መዋቅሮች እንዲሁም ሀብት በመጠቀም ሲመቸው የህዝብ ድምፅ እያጭበረበረ ሲያዳግተው እየነጠቀ የግል ሜዳው አድርጐ እየተጠቀመበት ለመሆኑ በተጨባጭ የታየ ነው
ይላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ‹‹ቀጣዩ ምርጫ ካለፉት የተለየ አለመሆኑን ያሳየው ገዥው ፓርቲ በራሱ ተቃዋሚዎች ኖሩም፣ አልኖሩም በምርጫው ላይ ብዙ ለውጥ አይኖርም በማለት በይፋ አረጋግጧል›› ሲል በመግለጫው አመልክቷል፡

ሌላው በመግለጫው ላይ የተጠቀሰው ‹‹መጪው ምርጫ ካለፉት የሚለየው ነገር ቢኖር ገዥው ፓርቲ በየመድረኩና በየአደባባዩ ከ5 ሚሊየን በላይ አባላት አሉኝ ቢልም ከእነዚህ አባላት ውስጥ ለአዲስ አበባ አስተዳዳር የሚመጥን ታማኝና ብቁ እጩ በማጣቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የምርጫ ዘመናቸው ሳያልቅ ህግ በጣሰ መንገድ የመጣላቸውን የህዝብ ድምፅ ትተው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ከሹመታቸው ተነስተው ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በእጩነት ማቅረቡና ምርጫ ቦርድም ከነበሩበት የህዝብ ተወካዮቻቸው በህጉ መሠረት መነሳታቸው ለህዝብ ሳያሳውቅ እጩነታቸውን መቀበሉ ነው›› ይላል፡፡ ‹‹መጪው ምርጫ በምርጫ

ስም የሚፈፀም ቧልት ነው›› ያለበትን ምክንያት በመግለጫው ሲያስረዳም ‹‹ገዥው ፓርቲና መንግሥት አንድ ግዜ አሸባሪ፣ ሌላ ግዜ የቀጠናው አተራማሽ ፀረ-ሠላም ኃይል አልፎም በሀገር ውስጥ በሠላማዊ ትግል ለለውጥ የሚታገሉ ኃይሎችን የእሱ ተላላኪ በማለት የሚከሰተውን ሻዕቢያ የኤርትራ መንግሥት ሳይጠየቅ እስከ
አሥመራ ድረስ ሄዶ ለማነጋገር ፈቃደኝነቱን ለዓለም በአደባባይ በገለፀበት የእኛን የምርጫ ሜዳ ይስተካከል ጥያቄ ወደጐን በማለት ያለተፎካካሪ የይስሙላ ምርጫ ለማድረግ መወሰኑ ነው›› ሲል በመግለጫው አትቷል፡፡

በመግለጫው ሲቀጥልም ‹‹ቦርዱ በምርጫ ህጉ መሠረት ተሳታፊዎች በእኩልነትና ያለአድልዎ የሚወዳደሩት የምርጫ ሂደት መኖሩን ማረጋገጥ ሲገባው ይህ ባለመሆኑ በህጋዊነት ከተመዘገቡ ፓርቲዎች ኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና አጋሮቹን ጨምሮ ይሳተፋሉ የተባሉት ከሲሶው ወይም ከ33 በመቶ የማይበልጡ በመሆናቸው በምርጫ መሳተፍ አሸንፎ ሥልጣን ለመያዝ መሆኑ ግልፅ ሆኖ ሳለ በ300 ተወካይ ለሚመሠረት ምክርቤት በአንድ ጣቢያ አንድ ወይም ሁለት እጩ በማቅረብ በሚደረግ ፉክከር የሚካሄድ የይስሙላ ምርጫ ነው›› ብሏል፡፡ ‹‹እስከዛሬ አንዱ ትልቁ ድክመታችን ወጣቶችን ለማብቃት የተደረገው ጥረት በተቃዋሚ ፓርቲዎች ሂደት ውስጥ ደካማ ነው፡፡ ምክንያቱም፤ አንዳንድ ቦታ የእኛም ሂደት ከገዥው ፓርቲ የተለየ ወይም የተሻለ አይደለም፡፡

ምንጭ ኢትዮቻነል ጋዜጣ የዛሬ ኤፕሪል 13 ዕትም

 

 

Previous Story

ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ሊገናኙ ይችላሉ

Next Story

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው? – ከገብረመድህን አርአያ

Go toTop