በኦሮሚያ ክልል የተደረገው ሰልፍ እንደውም የዘገየ ነው

April 2, 2023
በተያዙት መፈክሮች እንደተገለፀው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወይም የብልፅግና ስርሃትን አሻግሮናል፤ እንደግፋለን ነው።
ይሄ ስርዓት እኮ!

  •   ኢሬቻውን በደብረዘይት ማክብር የተቸገረ ከነበረ አልፎ አዲስ አበባ ድረስ አርቴፊሻል ሀይቅ ሰርቶ እንዲያከብር የካሰ ስርዓት ነው፣
  •   ለውጥ ስለጠየቀ ይታሰር ከነበር ወደ አሳሪነት የቀየረ ስርዓት ነው፤
  •    በወያኔ ተዘቅዝቆ ይገርፈው የነበረ ኦሮሞ ዘቅዝቆ እንዲሰቅል የፈቀደ ስርዓት ነው፤
  •   ኦሮሞ ያልሆኑትን ገድሎ ንብረት ሲያቃጥል በጠሚር ገና ጥቅሙን መቼ አስከበረ ተብሎ ያሞገሰ ስርዓት ነው፤
  •   ኦነግ ጥይት ጠሽ አድርጎ ጫካ መሮጥ ከነበረበት ዘመን እንደጫጩት እንዲጨፈጭፍ የፈቀደ ስርዓት ነው፣
  •   ከባንክ ጠባቂነት ወደ ባንክ ዘራፊነት የቀየረ ስርዓት ነው፣
  •   በቋንቋው መናገር ይሸማቀቅ ከነበረ ወደ እፃናት በግዳጅ ቋንቋውን እንዲማሩ ያደረገ ስርዓት ነው፤
  •    ከኦሮሞ ውጪ የሆነ ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እስከ ዶክተር እና ጀነራል እያፈነ አስሮ በድብደባ እያሰቃየ የካሰ ስርዓት ነው።
  •   ኦሮሞ አይደሉም ያሏቸውን መኖሪያ ቤት በስካቫተር እየናደ ቤት አልባ ያደረገ ስርዓት ነው፤
  •   ይሄ ስርዓት እኮ ለህክምና ከሀገር ለመውጣት ቋንቋ መናገርን መስፈርት ያደረገ ነው፤
  •   ይሄ ስርዓት እኮ ከተፈናቃይነት ወደ አፈናቃይነት የቀየረ ስርዓት ነው።
  •   መታወቂያ በማደል ሲቭል ሰርቪሱን የአንድ ብሄር ከለር የቀየረ ስርዓት ድጋፍ ማድረግ ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም።
❓❗ ችግር የሚሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ሌላው ሲረገጥለት ለመደሰት ነበር ወይ የሚል ጠያቂ ሲመጣ ነው።
❓❗ ችግር የሚሆነው በዚህ መልኩ የአንድ ሀገር ህዝቦች መሆን እንችላለን ወይ የሚል ጠያቂ ኦሮሞ ሲመጣ ነው።
❓❗ ችግር የሚሆነው ተበቃይ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን ማሰቢያ ሲያሰፋልን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ተዓይን ጆሮን የማመን ደዌ! – በላይነህ አባተ

Next Story

የተካደው የፕሪቶሪያ ስምምነት… – ሙሉዓለም ገ/መድኀን  ከሁመራ-ጎንደር

Go toTop