ጉዳዩ ዘረኝነት ያሳበደው ፖለቲካዊነት የወለደው ነው። ጠሚ ዐቢይ ሚኒስቴር መሾም ብቻ ስላልበቃኝ ድስት የደፉ ከለባትንም መሾም አለብኝ በማለት እንደዚህ ነውር ሠርቷል። ታሪክም እግዚአብሔርም ይቅር አይለውም።
አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ እንጠብቃለን።
ከዚችም ከዚያችም የወለዷቸውን ልጆች አስኬማቸውን አስረክበው ትዳር መሥርተው ወይም በሕግ ተገድደው ሊያሳድጉ የሚገባቸውን ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን ክብር ብለን ዝም ማለታችን እዚህ አደረሰን።
![ኦርቶዶክስ እነድትድን እንድትከበር ከተፈለገ መጀመሪያ ከባርነት ከፍርሀት እና ከአደርባይነት መላቀቅ ይጠበቅባታል። ለመጣው ለሄደው ጎንበስ ቀና ማለት ባርነትን ተቀብሎ በጭቆና የመኖርን ባህል መስበር ይጠበቅባታል::](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2023/01/326730830_706001091232236_1376427820319302681_n.jpg)
ዓባይነህ ካሤ – ዲን
ጉባኤ ከለባት!