የፍትሕ ቢሮው ለአቶ ሠማ ጥሩነህ ማስጠንቀቂያውን የሠጠው የኢትዮ 360 ሚዲያ ቅዳሜ መስከረም 8/2015 የአቶ ሠማን የትምህርት ማስረጃ ማጭበርበር አስመልክቶ በሠጠው ጥቆማ መነሻነት ተመስርቶ መሆኑ ተሰምቷል።
የፍትህ ቢሮው የሙስና ወንጀሉን ማጣራት ከመጀመሩ በፊት አቶ ሰማ ተምሮበታል ከተባለው የቻይና ዩንቨርስቲ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ ተምሮ የተሠጠው የ(PHD) የምስክር ወረቀት ካለ በኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የአቻ ግምቱን በማሠራት እስከ መስከረም 12/01/2015 ዓ/ም ማስረጃውን ለሶስት ተቋማት እንዲያስገባ አዝዟል።
በዚህም አንደኛ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮው፣ ሁለተኛ ለክልሉ ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን፣ ሦስተኛ ለክልሉ የብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማረጃውን የማያቀርብ ከሆነ ምርመራ ማጣራት እንደሚጀምር ማስታወቁ ተሠምቷል።
ይህንን የሠሙ የትምህርት ማስረጃ ያጭበረበሩ ሌሎች ባለ ስልጣናት ጭምር ጭንቅ ውስጥ መግባታቸው ታውቋል።