አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ!

July 31, 2022

እንደ ዋላ ውሀ እደጠማት
እንደራባት ጥም እንደያዛት

የሚያሳብቀው ገላዋ
ጎስቋላ ነው ስጋዋ

ይህቺ እማማ…..

አዲስ አቁማዳ ተሸክማ
አየኋት ማህሌት ቆማ

አዳዲስ ዜማ ስታዜም
ስትደረድር ስትገጥም

አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅልኝ
የወይን አረግ ጥመቅልኝ

እባክህ ውዴ ….

እንጀራዬን ልጋግረው ላስፋ
ፍለቅ እባክህ የኔ ተስፋ

ዳኘው ገበታየን
ጎብኘው ቃል ኪዳኔን

ብይኔን ክፈት ደጁን
የማይ መቅጃየን የምንጩን

ላጠጣ አብራኬን ላርካ
ልዘምርልህ እጄን እንካ

የምስጋና ነዶ ይዤ
እቅፍ ሙሉ አበባ አስይዤ

ከከፍታው ተራራ ላይ አወጣለሁ
ስእለቴን እከፍላለሁ

እያለች ማህሌት ይዛለችና
ክፈትላት እባክህ ራራና

አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅላት
ቆማለችና ተለመናት
እባክህን ፍለቅላት
ተገለጥማ እሺ በላት

እባክህን እባክህን
እባክህን እባክህን
እባክህን ብዬ ስልህ?

ሀምሌ፣ 2014

Geletaw Zeleke

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በየሰብአዊ እርዳታ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ያልተፈቀደ ጥሬ ገንዘብ እና ቁሳቁሶችን የማስተላለፍ ተግባርን በጽኑ አወገዘ

Next Story

የአልሸባብ የጥቃት ሙከራ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን  ለቀጠናውና ለምእራቡ አለምም የማስጠንቀቂያ ደወልነው

Go toTop