♦የከተማው ሸኔ አራት ኪሎ ቁጭ ብሎ እያፈነ ይሰውርሃል!!
♦የጫካው ሸኔ እያረደ ይጥልሃል ተናቦ መስራት ይልሃል ይኸው ነው!!
ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማሪያም – የአብን የፅ/ቤት ኃላፊ
የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከብዙ እግር ጉተታ በኋላ ዛሬ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም በአስቸኳይ ስብሰባ ያሳለፈው ውሳኔ በመላው ዓለም ፊት ሀገራችንን መሳቂያ የሚያደርግ አሳፋሪ ውሳኔ ነው። በተለይም በኦሮሚያ ፣ በቤኒሻንጉልና በሌሎች ክልሎች በግፍ ለሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ እንደ ታላቅ ታሪካዊ ክህደት የሚቆጠር ነው።
1. “ኢሰብአዊ ድርጊት” ፣ “ኢሰብአዊ ጭፍጨፋ” በማለት በብሔር ማንነት ላይ የተመሠረተ የዘር ፍጅት (genocide) መደረጉን ክዷል ፤
2. ‘ንፁሃን ዜጎች” ፣ “ሲቪል ዜጎች” በሚል ሽፋን የጥቃቱ ቀንደኛ ዒላማ የሆነውን የአማራ ህዝብን ሆን ብሎ ሳይጠቅስ አልፎታል ፤
3. “በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች” በማለት በተለይ መረን የለቀቀ የዘር ማጥፋት ማዕከል የሆነውን የኦሮሚያንና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ሳይጠቅስ ፣ በየክልሉ ጥፋትን በእኩልነት በማከፋፈል አልፏል ፤
4. “ባለፉት 27 ዓመታት የተዘራው የዘር ጥላቻ” የሚለው አሳሳች ሀረግም በአሁኑ ወቅት ከቁጥጥር ውጭ ለሆነው የዘር ማጥፋት ድርጊት ቀንደኛ ተጠያቂ የሆነውን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ነፃ ለማውጣት የታለመ ነው ፤
5. የተፈፀመውን ድርጊት “እጅግ በጣም በመኮነን” ፣ “በጣም በመኮነን” የሚለውም የተለሳለሰ አገላለፅ ሆን ተብሎ ድርጊቱን በጥብቅ ላለማውገዝ የተደረገ ነው ፤
6. ውሳኔው በህግ ተጠያቂ የሚያደርጋቸው “ግለሰቦችን” እንጂ በአሸባሪነት የተፈረጁ የታጠቁ ቡድኖችና የነሱ ሽፋን ሰጭ የሆኑ የፖለቲካና የሚዲያ ድርጅቶችና ተቋማትን አይደለም ፤
7. የሀገሪቱ የመጨረሻ ሥልጣን አካልና አስፈፃሚውን የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት ፓርላማ የፌዴራሉም ሆነ የክልል መንግሥታት ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለመጠየቅ እንኳን አልደፈረም ፤
8. ፓርላማው ጥቃቱን በስሙ ጠርቶ ሳያወግዝ ፣ የብዙ ሺህ አማራዎችን ህይወት እየቀጠፈ ላለው የዘር ማጥፋት ድርጊት ማንንም ተጠያቂ ሳያደርግ ፣ “ዜጎች” እያለ ስምና መልክ ለነፈጋቸው የጥቃቱ ሰለባ ህፃናት ፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ህይወት የሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ማድረግና የብሔራዊ ሀዘን ቀን በመንፈግ ኢሰብአዊ ስብስብ መሆኑን አሳይቷል ፤
9. ይህ በታሪክ እጅግ አሳፋሪ ተደርጎ የሚመዘገብ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፖለቲካ ተውኔት ፣ ፓርላማው በሀገሪቱ የበላይ ህግ እንደተሰጠው ውክልናውም ሆነ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለገዥው ፓርቲና መንግሥት መሆኑን በይፋ ይመሰክራል።
ወንድሜ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከጀርባህ ለነፃነት ፣ ለፍትህና ለክብር የቆምን ብዙ ሚሊዮን አማሮች አለን ‼️