![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/01/CE-logo.jpg)
በደብዳቤው ዳይሬክተሩ የድርጅቱን መርህ በመጣስ ከሙያ ስነ ምግባርና ከገለልተኝነት ውጪ እየፈጸሙት ስለሚገኘው ከስነምግባር ውጭ የሆኑ ተግባራት አስረድቷል።
ዳይሬክተሩ የሚያካሂዱት ህገ ወጥ ተግባር የተባበሩት መንግሥታትን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት መሆኑን አመልክቶ በኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀውን ድርጅት ሽፋን በመስጠት በሚያከናውኑት ተግባር ላይ ምርመራ እንዲደረግ ክስ አቅርቧል።
“ማንኛውም ሰው በእምነቱ፣ በቆዳው ቀለምና በአካባቢው ምክንያት ጤናው የመጠበቅ መብቱን ሊያጣ አይገባም” የሚለውን የዓለም ጤና ድርጅት ህገ መንግሥታዊ መርህ በመጣስም ዳይሬክተሩ የተወለዱበት አካባቢን ችግር ብቻ በመጥቀስ በአሸባሪው የተፈጸሙ ወንጀሎችንና የጤና ተቋማት ውድመቶችን መደበቃቸውን ገልጿል።
በአፋርና አማራ ክልሎች በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት የደረሱ ከፍተኛ ጥፋቶችን በመሸፈንም ወደ ትግራይ ክልል ሰብኣዊ ድጋፍ እየገባ አይደለም በሚል ስልጣናቸውን ተጠቅመው ክስ እያቀረቡ መሆኑን አስገንዝቧል።
በአማራና አፋር ክልሎች ስለወደሙት ከ500 በላይ የጤና ተቋማት እና ከ1 ሺሕ 700 በላይ የጤና ጣቢያዎች ያሉት ነገር አለመኖሩንና በዚህም ሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ ምርመራ እንዲያካሂድ አሳስቧል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በተለይም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በኩል የዓለም ጤና ድርጅትን መርህ በመጣስ የሚያካሂዱትን የወገንተኛ እንቅስቃሴ ቦርዱ በማስረጃነት ተጠቅሞ ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቋል።
FBC