ለሀገር ብሎ ከሚሰራው ስራም አይደናቀፍም። ሀቅን መቀበል እና የእውነት የተሰማውን የማይናገር ካለ ግን እሱ ሌላ ነው። እኛ መንግስትን የምንደግፈው እንደ ፓርቲ ሳይሆን እንደሰለጠነ የዲሞክራሲ ሀገራት ሲሰራም ልናመሰግነው ልንተባበረው፣ ሲያበላሸውም ልንነቅፈው ልናርመው ነው እንጂ በጭፍን አንደግፍም፣ በጭፍንም አንቃወምም ሁሉም በምክንያት ነው።
ይህን ያለመደ ካለ ገና ከካድሬነት አውቶብስ የተሳፈረ መንገደኛ ነው። ለሁሉም ዲያስፖራውን ወክላችሁ ለተገኛችሁ ቅሬታችሁን እንዲህ ድምፃችንን በማሰማታችሁ እጅግ ደስ ብሎናል። የቴክሳስ ቡድን ከዲሲ ቀጥሎ ሁሌም በሀገሩ ጉዳይ አይደራደርም። መንግስት ይህን በማወቁም ደስ ብሎናል። #ተንፍሷል ብሏል መንግስቱ።