በቁጥጥር ስር የዋለው የእህል በረንዳው የእሳት አደጋ
ጥቅምት 20/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ፀጋ አብ ህንፃ ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ከ1 ሰዓት በፊት ዋልታ የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች እየተረባረቡ እንደሚገኙ መዘገቡ ይታወሳል።
በቀጣይም የእሳት አደጋውን መንስኤ፣ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ እንደሚሰጡ የከተማዋ ፕሬስ ሰክሪታሪያት አሳውቋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ እህል በረንዳ አካባቢ አማኑኤል ፀጋ አብ ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ።
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ወጣቶች እየተረባረቡ ይገኛሉ።