ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፣ ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተከናወነ ያለውን እረፍት አልባ የሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም አድንቀዋል፤ ምስጋናም አቅርበዋል።
ጄነራል መኮንኑ በጉብኝቱ ወቅት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው ብለዋል።
አክለውም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚንቀሳቀሱ የውክልና ጦር አስፈፃሚ ቅጥረኛ ኃይሎች መቼም አይሳካላቸውም ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
EBC