በግምባሩ የተገኙት ም/ጠ/ኢታማዦር ሹሙ ፣ ለምንም የማይበገረው ሠራዊታችን ከቀደምት የኢትዮጵያ ታሪክ በመነሳት ለህይወቱ ሳይሳሳ በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አሸባሪ ሀይል ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ኦፕሬሽን አድንቀዋል።
ጀነራል አበባው ፣ ሠራዊታችን በተደጋጋሚ የሚያስመዘግባቸው ድሎች የሽብርተኛውን ሀይል ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመሆኑ ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀምም የወትሮ ዝግጁነት አቅም የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ፣ ሰራዊታችን ህዝባዊነት ባህሪውን አስጠብቆ አሸባሪውን ሀይል አንገት እያስደፋ የወረራቸውን አንዳንድ ቦታዎች በማስለቀቅ አኩሪ ታሪክ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በህዝብ ላይ እያሳደረ ያለውን ግፍና በደል በመገንዘብ በአጭር ጊዜ እርምጃ በመውሰድ የተፈናቀለውን ማህበረሰባችን ወደ ቀየው እንዲመለስ ለማድረግ ግምባር ላይ ያለው ሀይላችን የጠላትን ቅስም እየሠበረ ነው ብለዋል።
ተቋሙም በአሁኑ ሠዓት ብቁ ሠራዊትን በማፍራት አስተማማኝ የዝግጁነት ምዕራፍ ማጠናቀቁንም ተናግረዋል።(ኢፌድሪ መከላከያ)
–(ኢፌድሪ መከላከያ)