3500 ሜትሪክ ቶን ምግብ እና ህይወት አድን የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ከ100 በላይ የጭነት መኪኖች በሠላም መቐለ መድረሳቸውን በአለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ አስታውቋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎትን ለመሸፈን የአለም ምግብ ፕሮግራም እና አጋር የረድኤት ድርጅቶች አስፈላጊውን አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉም ቢሮው አስታውቋል።
አሸባሪው የህወሓት ጁንታ በአማራና እና አፋር ክልሎች ላይ ወረራ መፈጸሙን ተከትሎ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱ መስተጓጎሉ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።
EBC