እኛ በበርሊንና አካባቢዋ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በቅርቡ በነሀሴ 31 እስከ መስከረም 04 ቀን 2020ዓም በሀገራችን ኤምባሲ ላይ የተፈፀመዉን ብሄራዊ ዉርዴት በተመለከት ሰሞኑን በበርሊን ከተማ ዉስጥ በተከታታዩ ቀናቶች በግልም በቡድንም ስለሁኔታዉ ሰፊ ዉይይት ስናደርግ የቆየን ሲሆን በትናንትናዉም እለት የኢትዮ በርሊን የኢትዮጵጵያዉያን ማህበር አባላት በበርሊን ከተማ በሚገኜዉ ሉትዞዉ ፕላትዝ መናፈሻ ዉስጥ በመሰብሰብ የአጸፋ እርምጃ ለመዉሰድ የወሰኑ ሲሆን። ዛሬ ደግሞ በዚህ ቦታ ይህንን የጋራ መግለጫ ቋንቋ፣ ኃይማኖት፣ እንዲሁም ሌሎች ከኢትዮጵያዊነታችን ቀጥሎ የምናያቸዉ ማንነቶች ሳይገድቡን አዉጥተናል።
እንደሚታወቀዉ ላለፉት ሰላሳ አመታት ሀገራችንን በሁለንተኛዊ ደረጃ በሚባል መልኩ ቀድመዉ ከነበሩብን ችግሮች በተጨማሪ የጎሳ ፖለቲካዉን ወደ ሀገራችን የፖለቲካ አስተሳሰብ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ መጠነ ሰፊ ዉድመት በመድረስ ላይ ይገኛል። ይህንን በመቃወም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫፍ ጫፍ አቅሙ በፈቀደ ሁኔታ ሲታገል የነበር ሲሆን የነበረዉን ስርአት አስወግዶ ወደ ለዉጥ መንገድ እየሄድን ነዉ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በሀገራችን ጎሳንና ኃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ዉድመቶች እየደረሱ ይገኛሉ። እኛ እንደተለመደዉ የሚደርሰዉን ዉድመት የትኛዉም የፖለቲካ ኃይል ይፈፅመዉ እናወግዛለን። በተለይ አሁን ያለዉ አዲሱ መንግስት የህግ የበላይነትን እንዲያመጣ ከድጋፋችን በተጓዳኝ ስንወተዉት የነበረ ሲሆን ይህ ባለመደረጉ ምክንያት አሁን ወዳለንበት ዉጥንቅጥ ችግር ልንገባ ችለናል።
ከዚህ በፊት የደረሱትን እልቂቶች ተገቢዉ ባለ ድርሻ አካላት መርምረዉ ወደ ተገቢዉ ፍርድ እንደሚያደርሱት ተስፋ እያደረግን በቅርቡ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በተቀሰቀሰ ጎሳንና ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ ዉድመት ለጆሮ የሚዘገንኑ ወንጀሎች ተፈፅመዋል። ከተሞች ከነ ሙሉ ንብረታቸዉ ተቃጥለዋል፣ ሰዎች አካላቸዉ በስለት በመቆራረጥ ተገድለዋል፣፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ህፃናት ወላጅ አልባ ተደርገዋል፣ እንዲሁም ሌሎች በዚህ ዘመን ይፈፀማሉ የማይባሉ ድርጊቶች በሀገራችን ተፈፅመዋል። ይህ ወንጀል ሲፈፀም የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አስከባሪዎች ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም ነበር። በተመሳሳይ በሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገር የሚገኙ ፅንፈኛ ሚዲያዎች ከዚህ ድርጊት ቀደም ብሎ እንደሚያደርጉት በእልቂቱ ላይ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነበር።
ይህንን እልቂት ተከትሎም ያለዉ መንግስት እጅግ ቁጥራቸዉ ትንሽ የሆኑ የወንጀል ተጠርጣሪ ግለሰቦችንና እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸዉን ሰዎች ማሰር ሲጀምር በዉጭ ሀገር የሚገኙ ይህ ወንጀል እንዲፈፀምና እንዲስፋፋ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ኃይሎች ግንባር ገጥመዉ የዲፕሎማሲያዊ የበላይነት ለማግኜት መጠነ ሰፊ የማምታታት እና ዓለም አቀፍ ማሀበረሰብን አቅጣጫ የማስቀየር እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ። ለአብነት ለመጥቀስም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን መዉረር፣ የተቃዉሞ ሰልፎችን ማድረግ፣ ወንጀል የተፈጸመባቸዉን የእኛን ወገኖች ፎቶዎች በመያዝ፣ በማሰራጨት ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል ጩኸት ማሰማት፣ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን እንደ ፖለቲካ እስረኛ እንዲታዩ መቀስቀስና የመሳሰሉትን ማዘናጊያዎችን ሲፈፅሙ ከርመዋል። በተለይ በቅርቡ በመስከረም 31 ቀን 2020 ዓም በበርሊን ከተማ የሚገኜዉን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ጥሰዉ በመግባት የሀገራችንን ባንዲራ በዉርዴት በማዉረድና በመቅደድ በሌላ የኦሮሞ ነጸነት ግምባር አርማ በመተካት የሀገራችንን ክብርና ልአላዊነት ደፍረዋል። በዚህ ድርጊትም በየ ደረጃዉ ተጠያቂ የሚሆኑ አካላትን ይህ ጉባኤ እንደየ አስፈላጊነቱ የሚጠይቅ ሲሆን የሚከተሉትን የአፀፋ እርምጃዎች ለመዉሰድ ተስማምተናን።
- በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ዉስጥ ሁነዉ የተሰጣቸዉን ሀገራዊ ኃላፊነት ባለመወጣት የሀገራችንን ክብር ለማዋረድ ከሚሰሩ ኃይሎች ጋር የሚመሳጠሩ ግለሰቦች ከሀላፊነታቸዉ እንዲነሱና በምትካቸዉ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል አመለካከት ያላቸዉና ብቃት ያላቸዉ ሰራተኞችና ዲፕሎማቶች እንዲተኩ።
- የህግና የስርእት አገር በሆነችዉ ጀርመን አገር ዉስጥ የሚገኜዉ ኤምባሲአችን በቪየና አለም አቅፍ ስምምነት 1961 አንቀፅ 22 መሰረት ይህ ዉርዴት ሲፈጸም የጀርመን ፖሊስ ኃይል ጥበቃና መከላከል ባለማድረጉ የምንጠይቅ ሲሆን በተጨማሪም በዚህ ወቅት የተደረገዉን የተቃዉሞ ሰልፍ ያስፈቀዱ እና ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን ላይ የጀርመን ፖሊስ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።
- በቅርቡ በመስከርም 18 ቀን 2020 ዓም ከጧቱ 04፣00 ሰእት (10፣00 ) የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል የምንል ኢትዮጵያዉያን በበርሊን ከተማ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ጽንፈኛ ኃይሎች በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመዉን ወንጀል ለመደበቅ ያደረጉትን ድርጊት ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ
የሚያጋልጥ ሰልፍ ለማድረግ በሙሉ ድምፅ ተስማምተን ወስነናል።
ኢትዮጵያ በክብር ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!!
በርሊን
መስከረም 06 ቀን 2020 ዓም