እኔ ማነኝ / ግርማ ቢረጋ ስቶክሆልም ስዊድን

September 8, 2019

ቁጭ ብዬ አንድ ሌሊት
ሳሰላስ በዋልኩበት ።

አንደበቴ ቃል አውጥቶ
በእራሴ ላይ ተነሳስቶ ።

ቢጠይቀኝ ማንህ አንተ
ብሎ ቢለኝ እያቃተተ ።

መልስ አጣሁኝ ምን ልበለው
ባዶነቴን የማስበው ።

እንዴት ልሁን እኔ ራሴ
ከራሴው ጋር መካሰሴ ።

ነኝ ወይ እኔ አንድ ሙሉ
ወይስ ባዶ እንክብሉ ።

የማልሆነውን የሆንኩ
በባዶ ቤት የተኮፈስኩ ።

ደሞ ጉራ ህልም የሌለው
ለራሴ እንኳን የማይገባው ።

ባዶ ቀፎ የድምፅ አልባ
ጥላት እረሴን የምቀባ ።

ላይ ያልወጣው ታች ያልወረድኩ
ድክመቴንም የመሰከርኩ ።

ሆኜ ስገኝ ጫፍ የሌለኝ
በተፈጥሮ የማልቀኝ

ጭልጥ ያልኩኝ ምን የሌለኝ
ከሰው ሁሉ እኔ እኮ ነኝ

ንገሩኛ እኔ ማነኝ ።
ሴፕቴምበር 2019

Previous Story

‘የበታችነት ስሜት’ እግዚአብሔር ይማርህ የማይሉት በሽታ (በገ/ክርስቶስ ዓባይ)    

Next Story

ሸበረኸ እንቁጣጣሽ! – በላይነህ አባተ

Go toTop