የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=SvwytfrDZTg&t=73s
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ A 77608 በሆነ «አቶዝ» የቤት መኪና በባለሙያ በመፍታት ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረየስ ጠብመንጃዎች ጥር 28 ቀን 2011 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አዲሱ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና ከአማራ ብሄራዊ ክልል አዊ ዞን እንጅባራ ወረዳ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 53119 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከከሰል ጋር በመጫን 46, 404 ልዩ ልዩ የሽጉጥ ጥይቶች ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ/ም ከለሊቱ 9፡20 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አጂፕ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ከሦስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡