የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

January 16, 2019

የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=epx_GOJUaUQ
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለሃገሪቱ የቱሪዝም እድገት የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ድርጅት ጠይቋል፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር ትናንት በተካሄደው ውይይት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሌንሴ መኮንን እንደገለጹት፣ ቱሪዝም ያለ ኪነጥበብ ባለሙያዎች እድገቱን ማፋጠን አዳጋች ነው፡፡ ከቱሪዝም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ኪነ ጥበብ ሀገራዊ ወግ ባህልና እሴቶችን በማስተዋወቅና ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

የድርጅት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሰርፀ ፍሬስብሃት በበኩላቸው፣ ኪነ ጥበብ የቱሪዝም ዘርፍ በማሳደግ የላቀ ሚና እንዳለው ጠቁመው፣ ለዚህም ተቋማቸው በአዲስ መልክ የተጠናከረ ስራ ለመስራት እቅድ መያዙን አንስተዋል፡፡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም በጥበብ ስራቸው ውስጥ የሀገሪቱን መለያ/ብራንድ /እና ልዩ ልዩ እሴቶችን በማስተዋወቅ ለቱሪዝም ዘርፉ የላቀ ሚና ማበርከት እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

Previous Story

በምዕራብ ኢትዮጵያ ህገ ወጥ ትጥቅ ታጥቀው የህዝቡን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 835 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የምእራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ

Next Story

የሲሲዲ መኖሪያ መንደር መስራች ፍርድ ቤት እንዲቀርበ ታዘዘ

Go toTop