በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑን ገለጸ:: ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ መሰራት ያለባቸውን ተግባራት ለማከናወን ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቅቄ; በሰው ሃይል የማደራጀት እና በስፋት ወደ ስራ ማስገባት እንቅስቃሴ ልገባ ነው ብልውል::
https://www.youtube.com/watch?v=aVUdalQQ5Mk&t=54s
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደተናገሩት ኤጀንሲው ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ይሰራል። የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ በዋናነት የዲያስፖራ ማህበር ልማት፣በመዋዕለ ነዋይ ፍሰት፣በእውቀት ሽግግር፣በበጎ አድራጎት፣በሀብት ማሰባሰብ እንዲሁም በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን መብት በማስጠበቅ ላይ ያተኩራል። ኤጀንሲው በቅርቡም በዳያስፖራው ማህበረሰብና በባለድርሻ አካላት በግልፅ ታውቆ ስራውን በይፋ ለመጀመር የመክፈቻና የትውውቅ መርሃ ግብር እያዘጋጀሁ ነውም ብሏል::